ቤንዚን በሊትር 10 ብር ጨመረ።
በተጨማሪም በተለያዩ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተነግሯል።
ይህንን የተናገረው የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው፡፡
በተደረገው መሻሻያ መሰረትም ቤንዚን በሊትር 10 ብር ጭማሪ አሳይቷል፡፡
በዚህም 91 ብር 14 ሳንቲም የነበረው ቤንዚን 101 ብር ከ47 ሳንቲም ሆኗል፡፡
90 ብር ከ28 ሳንቲም የነበረው ነጭ ናፍጣ 98 ብር ከ 28 ሳንቲም ሆኗል፡፡
90 ብር ከ 28 ሳንቲም የነበረው ኪሮሲን 98 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል፡፡
100 ብር ከ 2 ሳንቲም የነበረው ቀላል ጥቁር ናፍጣ 5 ብር ጨምሮ 105 ብር ከ97 ሳንቲም ሆኗል፡፡
የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር ከነበረው 77 ብር ከ76 ሳንቲም የነበረው 109 ብር ከ56 ሆኗል፡፡
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር "በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ይሠራል” በሚል ተስፋ ነዳጅ ይዘው የተደበቁት ቦቴዎች አግኝቻለሁ ማለቱ ይታወሳል።
ጭማሪው ከዛሬ ታህሳስ 29፣2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comentarios