ታህሳስ 4፣ 2015- "በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሌላ ክልልን ሰንደቅ ዓላማ ማውለብለብ እና መዝሙር ማዘመር ህጋዊ መሰረት የለውም"
- sheger1021fm
- Dec 13, 2022
- 1 min read
በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሌላ ክልልን ሰንደቅ ዓላማ ማውለብለብ እና መዝሙር ማዘመር ህጋዊ መሰረት የለውም ሲል የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡
ሁኔታው የፌዴራል ሥርዓቱን መሰረታዊ መርህን ይጥሳል ብሎታል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ጉዳዩን አንድ ብሄር በሌላው ላይ የበላይነት ለማምጣት እየተሰራ እንዳለ በማስመሰል የሚቀርበው ሃሳብ ፍፁም የተሳሳተ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ማንኛውንም አይነት ጥያቄና ሃሳብ በመመካከርና በውይይት እንጂ በሁከትና በትርምስ አይሆንም ብለዋል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments