top of page

ታህሳስ 4፣2017 - ''የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ሰዎች፤ በህገ-ወጥ ስራ ተሰማርተው ስለደረስኩባቸው እርምጃ እየወሰድኩ ነው'' የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

  • sheger1021fm
  • Dec 13, 2024
  • 1 min read

''ህጋዊ የመኖሪያም ሆነ የስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በርካታ የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ሰዎች፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በህገ-ወጥ ስራ ተሰማርተው መገኘታቸውን ስለደረስኩባቸው የተለያየ እርምጃ እየወሰድኩ ነው'' ሲል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተናገረ፡፡


ዘመድ ለመጠየቅ በማስመሰል ከዱባይ፣ ከኤርትራና ከኡጋንዳ በመመላለስ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦችን በሻንጣ በማስገባትና በማስወጣት የኮንትሮባንድ እና ሌሎች ህገወጥ ተግባራትን ሲከውኑም ተገኝተዋል ብሏል በላከልን መግለጫ፡፡


በሌሎች ሀገራት ከሚገኝ ህገ-ወጥ ደላሎች ጋር አብረው በመስራትም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ሲከውኑ የተገኙም አሉ ብሏል፡፡


በተጨማሪም ለህገ-ወጥ ተግባር የሚያገለግሉ ሐሰተኛና የተጭበረበሩ የጉዞና የይለፍ ሰነዶችን ማህተሞ፣ የባንክ ደብተሮችን በማዘጋጀትና በመጠቀምም ህገ-ወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ ተገኝተዋል ይላል መግለጫው፡፡


የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው ጥገኝነት ያላገኙ እና ከተፈቀደው የ90 ቀናት የቆይታ ጊዜ በላይ በኢትዮጵያ እየቆዩ ነው የተባሉ ኤርትራዊያን ሐሰተኛ ሰነድን እንዲሁም ሀሰተኛ ማንነትን በመጠቀም ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሲያከናውኑም ተገኝተዋል የተባለ ሲሆን ይህን ሲያደርጉ በመገኘታቸው የተለያየ እርምጃ መውሰዱን #የኢሚግሬሽንና_ዜግነት_አገልግሎት ተናግሯል፡፡


በዚህም ምክንያት መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶችን የፈፀሙ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ሁሉ እየወሰድኩት ባለው እርምጃ መሰረት ኤርትራውያንም ከሃገር እንዲወጡ እየተደረገ ነው ብሏል፡፡


ከሀገር ሲወጡም ያለፈቃድ ከ90 ቀን በላይ በኢትዮጵያ ለቆዩበት በህጉ መሰረት ለእያንዳንዱ ቀን 10 ዶላር እንዲከፍሉ ተደርጓል ብሏል፡፡


የተለያዩ #ኤርትራዊያን ከህግ ውጭ ሁለትና 3 አመት ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ተደርሶባቸው ከሀገር እንዲወጡ ሲደረግም ቅጣቱን መክፈል ግዴታቸው መሆኑ ይታወቅልኝ ብሏል አገልግሎት መ/ቤቱ፡፡


ይሁንና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በስደተኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ኤርትራውያን ዲፓርት እንደተደረጉ ተደርጎ የተሰራጫው መረጃ ሀሰት ነው ሲል አስተባብሏል፡፡


4,000 እና 5,000 ብር የመውጫ ቪዛ እንደተጠየቁ ተደርጎ የሚወራውም ከእውነት የራቀ ነው ብሏል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፡፡


የሚከፍሉት የመውጫ ቪዛ ሳይሆን ያለፈቃድ እዚህ ለቆዩበት ቅጣት ነው ብሏል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page