top of page

ታህሳስ 6፣ 2015- በኢትዮጵያ 68 በመቶ የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች እና 51 በመቶ የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ ጥናት አሳየ

  • sheger1021fm
  • Dec 15, 2022
  • 1 min read

በኢትዮጵያ 68 በመቶ የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች እና 51 በመቶ የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ ጥናት አሳየ።


ጥናቱ ያከናወነው ራይዝ ኢትዮጵያ በአለም ባንክ የሚደገፍ እና አለምአቀፍ የምርምር ፕሮግራም ሲሆን በትምህርት ጥራት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የተቋቋመ ድርጅት መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተናግሯል።


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቱት በጋራ በመሆን ጥትት እና ምርምሩን የሚያካሄዱ ተቋሟት ናቸው ተብሏል።


በዛሬው እለት የጥናት ውጤቱ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አዘጋጅነት በሂልተን ሆቴል ቀርቧል።


በኢትዬጲያ በተለያዩ የአንደኛ ደረጃ 168 ትምህርትቤቶች በሚገኙ በ 9,000 ተማሪዎች በተጠናዉ ጥናት መሰረት 2ኛ ክፍል ተማሪዎች 68% እና 3ኛ ክፍል ተማሪዎች 51% ያህሉ ማንበብና መጻፍ እንደማይችሉ ጥናቱ አሳይቷል።


የተማሪዎችን የትምህርት ዉጤት ለማሻሻል የትምህርት ስርአቱ የተናበበ እና የተቀናጀ ትግበራ አስፈላጊ እንደሆነ በጥናቱ ላይ ተጠቅሷል ተብሏል።


ንጋቱ ሙሉ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 
 
 

تعليقات


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page