top of page

ታህሳስ 6፣ 2015- የሴኔጋል መንግስታዊ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ገንዘብ ለምዝበራ እና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ ነበር ተባለ

  • sheger1021fm
  • Dec 15, 2022
  • 1 min read

የሴኔጋል መንግስታዊ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ገንዘብ ለምዝበራ እና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ ነበር ተባለ፡፡


የአገሪቱ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ገንዘብ ለምዝበራ፣ ለብልሹ አሰራር እና ለብክነት መጋለጡን ደርሼበታለሁ ያለው የሂሳብ አጣው መስሪያ ቤት እንደሆነ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡


የአገሪቱ የፍትህ ሚኒስቴር አስፈላጊውን እርምጃ ይወስድ ዘንድ አበክሮ መጠየቁ ተሰምቷል፡፡


የሂሳብ አጣሪ መስሪያ ቤት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያው ከተመደበው ገንዘብ የብዙ ሚሊዮን ዩሮ ግምት ያለው ምዝበራ መፈፀሙን አረጋግጧል ተብሏል፡፡


ምዝበራው የተፈፀመው በምርቶች እና በሸቀጦች ግዢ የተጋነነ ክፍያ እንደሆነ ዘገባው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page