top of page

ታህሳስ 7፣ 2015- በመንግስት ግዥና ጨረታ የሚሳተፉ አቅራቢዎች በገቡት ውል መሠረት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት ሊኖር ይገባል ተባለ

Updated: Dec 17, 2022



በመንግስት ግዥና ጨረታ የሚሳተፉ አቅራቢዎች በገቡት ውል መሠረት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት ሊኖር ይገባል ተባለ።


ይህ የተባለው በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን እንዲሁም በመንግስት ግዢ አገልግሎት አሰራር ዙሪያ በተካሄዱ የቁጥጥር ስራዎች የተለዩ ግኝቶችና የመፍትሔ ሃሳቦች ዙሪያ በአዳማ ይፋ በሆነበት መድረክ ላይ ነው፡፡


በሁለቱ ተቋማት አሰራር ዙሪያ ቁጥጥሩን አካሂዶ ግኝቶችን እና ምክረ ሃሳቦችን ለሚመለከታቸው በመድረኩ ይፋ ያደረገው የህዘብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ነው።


በመድረኩ ላይ ሲነገር እንደሠማነው በመንግስት ግዥና ጨረታ የሚሳተፉ አቅራቢዎች በገቡት ውል መሠረት ግዴታቸውን መወጣት ላይ ችግሮች አሉ።


የሚፈለገውን ዕቃ በወቅቱ ያለማቅረብ እና ጥራታቸው የተጓደሉ ምርቶችን ማስረከብ ከችግሮቹ መካከል እንደሆኑ ተነግሯል።


አቅም የሌላቸው አቅራቢዎች በመንግስት ግዢና ጨረታ እንዲሳተፉ የማድረግም ችግር እንዲሁ ተጠቅሷል።


ባሉት ቀነ ገደብ ዕቃዎችን የማያስረክቡ እንዱሉም ተነግሯል።

በወቅቱ በሚያስረክቡት ላይ በውሉ መሠረት እርምጃ ያለ መውሰድ ይታያልም ነዉ የተባለው።


አቅራቢዎችን ለመቆጣጠር ጠንካራ ስርዓት ሊዘረጋ እንደሚገባ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በምክረ ሃሳቡ ጠቅሷል።


ንጋቱ ረጋሳ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


bottom of page