ታህሳስ 7፣ 2015- የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በሀላፊነት ላይ የሚገኙትን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሣን በፍርድ ቤት መክሰሳቸው ተሰማ
- sheger1021fm
- Dec 16, 2022
- 1 min read

የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በሀላፊነት ላይ የሚገኙትን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሣን በፍርድ ቤት መክሰሳቸው ተሰማ፡፡
ዙማ በጆሃስበርግ ፍርድ ቤት በግል በራማፎሣ ላይ ክስ መመስረታቸውን በስማቸው የተቋቋመ ድርጅት እወቁልኝ ማለቱን ዘ ሳውዝ አፍሪካን ፅፏል፡፡
ጉዳዩ ከፋላ ፋላው አጋጣሚ ጋር የተገናኘ ነው ተብሏል፡፡
ከፕሬዝዳንቱ የፋላ ፋላ እርስት በውጭ ምንዛሪ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መዘረፉን ሸፋፍነዋል በሚል ሪፖርት ከወጣ በኋላ ራማፎሣ ጫና በርትቶባቸው ሰንብቷል፡፡
ፕሬዝዳንት ራማፎሣ የዙማን ክስ አይረቤ እና መሰረተ ቢስ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
በደቡብ አፍሪካ የገዢው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ANC የፖለቲካ ማህበር አገራዊ ሸንጎ ዛሬ መሪውን ይመርጣል ተብሏል፡፡
በጫና ውስጥ የከረሙት ሲሪል ራማፎሳ አንዱ ተፎካካሪ መሆናቸው ታውቋል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments