top of page

ታህሳስ 8፣ 2015- አገር አቀፍ የወጣቶች ምክር ቤት ለማቋቋም በተዘጋጀ የመነሻ ሰነድ ላይ በአዳማ ውይይት እየተካሄደ ነው

  • sheger1021fm
  • Dec 17, 2022
  • 1 min read

አገር አቀፍ የወጣቶች ምክር ቤት ለማቋቋም በተዘጋጀ የመነሻ ሰነድ ላይ በአዳማ ውይይት እየተካሄደ ነው።


የሚቋቋመው ምክር ቤት የወጣቶች ድምፅ በመሆን ለአባላቱ መብትና ጥቅም ይሰራል ተብሏል።


መንግስትን የማማከርና የመሞገት ሚና እንደሚኖረውም በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሙና አህመድ ተናግረዋል።


አገር አቀፍ የወጣቶች ምክር ቤት የማቋቋሙ አስፈላጊነት የታመነበት አሁን ባሉ የወጣት አደረጃጀቶች ላይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዳሠሣ ጥናት ከተካሄደ በኋላ እንደሆነ ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቅሰዋል።


እንደ እሳቸው አባባል አሁን ያሉ አደረጃጀቶች ለወጣቶች ድምፅ መሆን ላይ ክፍተት ይታይባቸዋል።


የአካታችነት ችግር እንደሚስተዋልባቸውም ሚኒስትር ዴኤታዋ የዳሠሣ ጥናቱን መነሻ አድርገው ተናግረዋል።


የሚቋቋመው አገር አቀፍ የወጣቶች ምክር ቤት ከፌዴራል እስከ ክልል ድረስ ተመሳሳይ መዋቅር ይኖረዋል ተብሏል።


የሌሎች ሀገራትን ልምድ ከግምት በማስገባት የሚቋቋም ምክር ቤት እንደሚሆንም ሠምተናል።


የውይይቱ ተሳታፊዎች ምክር ቤቱን ለማቋቋም በተዘጋጀው የመነሻ ሰነድ ላይ ሃሳብ እየሰጡ እንደሚገኙ ባልደረባችን ንጋቱ ረጋሣ ከአዳማ የላከልን መረጃ ያመለክታል።


ንጋቱ ረጋሳ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page