ታህሳስ 8፣ 2015- የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የአርብቶ አደሩና አርሶ አደሩን ስራ ለመደገፍ እስካሁን ከ9.7 ቢሊየን ብር በላይ ፋይናንስ አድርጌያለው አለ
- sheger1021fm
- Dec 17, 2022
- 1 min read

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የአርብቶ አደሩና አርሶ አደሩን ስራ ለመደገፍ እስካሁን ከ9.7 ቢሊየን ብር በላይ ፋይናንስ አድርጌያለው አለ።
ይንን ያህል ገንዘብ በማቅረብም በኢትዮዽያ ቀዳሚው ባንክ ሆኛለው ብሏል።
ባንኩ ከዓመታዊ ጉባኤው አስቀድሞ የሚያደርገውን የኅብረት ሥራ ማህበራት ቀንን በአዳማ አክብሯል።
የኅብረት ሥራ ማህበራት ቀኑ ለ4ኛ ጊዜ መከበሩን ከአቶ ደረጄ ወዳጆ የማህበራትና ደንበኞች ግንኙነት ዳይሬክተር ሠምተናል።
የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከ56 በመቶ በላይ የባንኩ ድርሻ በአርብቶና አርሶ አደሮች መያዙንና ባለቤቶቹም እነሱ መሆናቸው ተናግሯል።
በዝግጅቱ ላይ ሲነገር እንደሰማነው ባንኩ 9.7 ቢሊዮን ብር ለአርሶና አርብቶ አደሩ ስራ መደገፊያ ፋይናንስ በማድረግ በኢትዮዽያ ቀዳሚ ባንክ ሆኗል ተብሏል።
ገንዘቡ በግብርና ሜካናይዜሽን፣ በእህል፣ በቡና ምርት፣ በከብት እርባታ እና ማድለብ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለተሰማሩ ማህበራት፣ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች መቅረቡን ከአቶ ደረጄ ሰምተናል።
አርሶና አርብቶ አደሮች በማህበርና በዩኒየን ስር በመሆን ትልቁን የባንኩን ድርሻ እንደያዙ ተሠምቷል።
ባንኩ አንድ በመቶ ዓመታዊ ትርፉን የኅብረት ሥራ እና አርሶ አደሮችን ለማሰልጠን እንደሚያውልም ተነግሯል።
የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በ2021/22 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የኅብረት ሥራ ማህበራት የተለያየ እውቅና እና ሽልማትን ተሰጥቷል።
ቴዎድሮስ ወርቁ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
Comentários