በትይዩ(ጥቁር ገበያ) እና በባንክ የውጭ ምንዛሬ ተመን መካከል የነበረው ልዩነት መጥበቡ አስደስቶናል ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ተናገሩ፡፡
በቅርቡ ተግባራዊ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ አላማም ይህ እንደሆነም የብሔራዊ ባንክ ገዢው ጠቅሰዋል፡፡
አቶ ማሞ ምህረቱ ይህንን ያሉት፤ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. የተካሄደውን የልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ባደረገበት መግለጫ ነው።
በዛሬው ልዩ ጨረታ አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች አማካይ ዋጋ በአንድ ዶላር 107.9 ብር እንደሆነ ብሔራዊ ባንክ ተናግሯል።
ይህም ነገ ከነሐሴ 2፤2016 ዓ.ም ጀምሮ በዉጪ ምንዛሪ ተመን ላይ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ተጠቅሷል ።
በዛሬው ልዩ ጨረታ 27 ባንኮች ተሳትፎዉበታል ተብሏል፡፡
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ዉጤቱን ተከትሎ እንደተናገሩት "ተግባራዊ የተደረገዉን በባንክ ምንዛሪ ዋጋ እና በትይዩ የገበያ ዋጋ መካከል የነበረው ልዩነት መጥበብ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የዉጪ ምንዛሪ ጨረታዉን ከዛሬ ጀምሮ ሊያካሄድ መሆኑን እንዲሁም ፍላጎቱ ያላቸዉ ባንኮች በጨረታው መሳተፍ እንደሚችሉ መናገሩ የሚታወስ ነው፡፡
Comments