top of page

ነሀሴ 1፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • Aug 7, 2024
  • 1 min read

በናይጀሪያ በተቃውሞ ሰልፍ ወቅት የሩሲያን ሰንደቅ ዓላማ ሲያውለበልቡ ነበር የተባሉ 40 ያህል ሰዎች ተይዘው መታሰራቸው ተሰማ፡፡


በአገሪቱ የኑሮ ውድነቱን አልቻልነውም ያሉ ዜጎች በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርጉ መሰንበታቸውን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡


በሰልፎቹ ላይ የሩሲያን ሰንደቅ ዓላማ የያዙ ናይጀሪያውያን ተስተውለዋል ተብሏል፡፡


ከመካከላቸውም 40 ያህሉ ተይዘው ሲታሰሩ ይዘዋቸው የነበሩ የውጭ አገራት ሰንደቅ ዓላማዎችን እንደተቀሙ ተጠቅሷል፡፡


የአገሪቱ ጦር የበላይ በናይጀሪያውያን ሰልፍ ላይ የውጭ አገራትን ሰንደቅ ዓላማ ማውለብለብ ከአገር ክህደት ይቆጠራል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


ፕሬዘዳንት ቦላ ቲኑቡ ከግጭት አስከታይ የተቃውሞ ሰልፍ ይልቅ በጥሞና ብንነጋገር ይሻላል የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸው ታውቋል፡፡


የቱኒዚያው ፕሬዘዳንት ካይስ ሳኢድ በመጪው ምርጫ ለመወዳደር ማመልከቻ እና ተዛማጅ ሰነዶችን ማቅረባቸው ተሰማ፡፡


ካይስ ሳይድ ከማመልከቻቸው ጋር ከ242 ሺህ በላይ የድጋፍ ፊርማዎችንም እንዳቀረቡ አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡


ፕሬዘዳታዊ ምርጫው በመጪው ጥቅምት ወር እንዲካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል ተብሏል፡፡


የተፎካካሪነት ፍላጎት ያላቸው ማመልከቻ እና ተዛማጅ ሰነዶቻቸው እስከ ፊታችን ቅዳሜ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ተጠቅሷል፡፡


ያም ሆኖ የካይስ ሳኢድ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ይሆናሉ ተብለው ተጠብቀው የነበሩት ፖለቲከኞች በእስር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡


ምርጫው የሚካሄደው በአገሪቱ ፖለቲካዊ ውጥረቱ እየተካረረ በመጣበት ወቅት እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡



የአሜሪካዋ ምክትል ፕሬዘዳንት ካምላ ሐሪስ እና የምርጫ ተጓዳኛቸው ቲም ዋልዝ በጋራ የምረጡኝ ቅስቀሳ አደረጉ፡፡


ካምላ ሐሪስ እና ቲም ዋልዝ የጋራ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን ያደረጉት በፊሌዴልፊያ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡


በቅርቡ የሚከናወነው የዴሞክራቹ ብሔራዊ ጉባኤ የሐሪስ እና የተጣማሪያቸውን ይፋዊ እጩነት ያፀድቅላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡


የካምላ ሐሪስ የምርጫ ተጣማሪ ቲም ዋልዝ በአሁኑ ወቅት የሚኒሶታ አገረ ገዢ ናቸው፡፡


ካምላ ሐሪስ ከቀናቸው ቲም ዋልዝ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዘዳንት ይሆናሉ፡፡


በጥቅምቱ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ካምላ ሐሪስ የሪፖብሊካውያኑ እጩ ከሆኑት ከቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር እንደሚፎካከሩ መረጃው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page