በዚህም ሃገሪቱ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ልታገኝ እንደምትችል ተጠቁሟል፡፡
ወትሮውንም ቢሆን ግድቡን ለመገንባት ሲታሰብ ከሃገር አልፎ የጎረቤት ሃገራትንም ጭምር በኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል መሆኑ በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡
ግድቡ ሲጠናቀቅ ግማሽ ያህሉ ማለትም ከሚያመነጨው 5150 ሜጋ ዋት ከ2500ሜጋ ዋት በላዩ ለሽያጭ ሊውል እንደሚችል የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ሃይሉ አብርሃም ነግረውናል፡፡
ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ህዝቧ የኤሌክትሪክ ብርሃን ያየው ከ60 በመቶ ያልዘለለ እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡
አቶ ሃይሉ እንደሚሉት ከዚህ በኋላ የሃይል እጥረት ችግር አይሆንም ከዛ ይልቅ ግድቡ አልቆ በስፋት ሃይል ቢያመነጭም በተለይም ምንም ዓይነት ኤሌክትሪክ ለሌላቸው አካባቢዎች የሃይል ማሰራጫ መስመሮች መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡
በቂ ሃይል እያለ የኤሌክትሪክ የማያገኙ አካባቢዎች እንዳይኖሩ ዝርጋታው ቀጣዩ ትኩረት መሆን አለበትም ይላሉ፡፡
የግድቡ መጠናቀቅ በሃይል እጥረት ለሚሰቃዩት ትልልቅ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎችም መፍትሄ ይዞ እንደሚመጣ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ጎረቤቷ ኬንያን ጨምሮ ለሌላውም የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ እንደምትከውን ይታወቃል፡፡
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments