top of page

ነሀሴ 2፣2016 - የገበያ ቅኝት



ሰሞኑን የዶላር ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ ገበያው ለያዥ ለገናዥ እያስቸገረ ነው፡፡


አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ የገበያ ስፍራዎች ከዶላር ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው ምርቶች ድንገት ዋጋቸው ሲንር ተስተውሏል፡፡


መንግስትም #የዶላር_ጭማሪውን ተገን በማድረግ ዋጋ መጨመር አይቻልም፤ የሚጨምሩት ላይ እርምጃ እየወሰድሁኝ ነው ቢልም በነጋዴዎች ዘንድ ይህ እርምጃ ዋና አከፋፋዮቹን ሳይሆን ቸርቻሪው ነጋዴ ላይ ነው የበረታው ሲሉ እየተቹት ነው፡፡


በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ #ነጋዴዎች እንዳሉን ከሆነ ምርት አከፋፋይ ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል፤ መንግስት እነሱ ላይ እያደረገው ያለው ቁጥጥር የላላ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


ቸርቻሪ ነጋዴው ላይ ግን ቁጥጥሩ እጅግ የበረታ ነው ብለዋል፡፡


ታዲያ መንግስት አሁን እየሰራ ያለው አከፋፋዮችን ከመቆጣጠር ይልቅ ቸርቻሪ ነጋዴው ላይ ነው እየበረታ ያለው ገበያው እንዲረጋጋ ከተፈለገ ቅድሚያ #አከፋፋዮች እና አምራቾችን መከታተልና መቆጣጠር የዋጋ ንረት ችግሩን ይፈታል ብለዋል፡፡


ዘገባውን ለመስራት ከ02 እስከ ላምበረት ስንቀሳቀስ በተመለከትናቸው አብዛኛው ሱቆች ላይ የዘይት ምርት አለመኖሩንም ተመልክተናል፡፡


ጉዳዩን በተመለከተ ነጋዴዎችን ጠይቀን የነበረ ቢሆንም በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሚሰጠን ግን አላገኘንም፡፡


በአካባቢው ቅዳሜና እሁድ የዘይት ምርቶች መግዛታቸውን አንዳንድ ሸማቾች በመረጃ መልክ የነገሩን ሲሆን እጥረቱ ሰሞኑን የተከሰተ ነው ብለውናል፡፡


ምርቱ ከገበያ ከመጥፋቱ በፊት 5 ሊትር #ዘይት ከ1,180 ብር ጀምሮ እተሸጠ እንደነበር ሰምተናል፡፡


በዛሬው ገበያ ላይ አንድ ኪሎ ሽንኩርት ከ60 ብር እስከ 75 ብር ድረስ ተሸጠ ሲሆን ከቅዳሜና እሁድ ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቶበታል፡፡


ድንች በኪሎ 25 ብር ቲማቲም በኪሎ ከ20 ብር እስከ 25 ብር እየተሸጠ መሆኑን ተመልክተናል፡፡



በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page