ነሐሴ 10፣2015 - ዛምቢያ ከፍተኛ መጠን ወርቅ የጫነን የውጭ ሀገር አውሮፕላን ያዝኩ አለች
- sheger1021fm
- Aug 16, 2023
- 1 min read
የዛምቢያ የወንጀል መከላከል ሹሞች 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና ከፍተኛ መጠን ወርቅ የጫነን የውጭ ሀገር አውሮፕላን ያዝን አሉ፡፡
ከጥሬ ገንዘቡ በተጨማሪ 602 የተለያዩ የወርቅ ጌጣ ጌጦችንም ይዘናል ማለታቸውን አናዶሉ ፅፏል፡፡
6 ሽጉጦች እና በርካታ መሰል ጥይቶቻቸውም በአውሮፕላኑ ፍተሻ ወቅት ከተያዙት መካከል ናቸው፡፡
አንድ ዛምቢያዊ እና ዘጠኝ የተለያዩ አገር ዜጎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል፡፡
በግለሰቦቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የወንጀል መከላከል ሹሞቹ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
የኔነህ ከበደ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
YouTube: t.ly/SHEGER
Commentaires