top of page

ነሐሴ 13፣2016 - የቬሮኒካ አዳነ የሙዚቃ አልበምን በመላው አለም ለማከፋፈል ‘’ዞጃክ ወርልድ ዋይድ’’ የተባለ የሙዚቃ ኩባንያ ለድምፃዊቷ 160,000 ዶላር ከፈለ

በሚቀጥለው ሳምንት የሚለቀቀውን የቬሮኒካ አዳነ የሙዚቃ አልበምን በመላው አለም ለማከፋፈል ‘’ዞጃክ ወርልድ ዋይድ’’ የተባለ የሙዚቃ ኩባንያ ለድምፃዊቷ 160,000 ዶላር ከፈለ።


ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ "ስትል የሰየመችውን የመጀመሪያ አልበም በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚለቀቅ ተናግራለች።


የሙዚቃ አልበሙን ለመልቀቅ የታሰበው የፊታችን አርብ የነበረ ቢሆንም በህፃን ፌቨን አሰቃቂ ህልፈት ሀዘን ምክንያት ወደ ሚቀጥለው ሳምንት መዛወሩን ድምፃዊቷ ተናግራለች።


12 ሙዚቃዎችን የያዘው መጠሪያዬ አልበምን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሶስት ዓመት ፈጅቷል ተብሏል።


አልበሙ ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል፣ ሙሉ በሙሉ ወጪውም በራሷ መሸፈኑን ድምጻዊት ቬሮኒካ ተናግራለች፡፡

አልበሙ ስለፍቅር፣ ስለሰላም፣ ስለሀገር፣ ስለተስፋ እና ስለምስጋና የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ይዳስሳል ተብሏል።


ሙዚቃዎቹን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ሀላፊነት የወሰደው ዞጃክ ወርልድ ዋይድ መቀመጫውን በአሜሪካ ፍሎሪዳ ያደረገ ሲሆን በተለያዩ አለማት ማለትም ሜክሲኮ፣ ኢንዶኒዢያ፣ ጃማይካ እና ኬንያ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ይህ ካምፓኒ የኢትዮጵያን አልበም ሲገዛ የመጀመሪያው ነው ነው ተብሏል፡፡


መጠሪያዬ የተሰኘው አልበም በሚቀጥለው ሳምንት አርብ ነሀሴ 24፣2016 ቬሮኒካ አዳነ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ሲባል ሰምተናል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

Comments


bottom of page