ኩባንያው ይህን የተናገረው ትናንት ምሽት በኢትዮዽያ አገልግሎቱን ከጀመረው 17 ዓመት ከሞላው ከቪዛ ኩባንያ ጋር አብሮ መስራት መጀመሩን በተናገረበት ጊዜ ነው።
ይህን ተከትሎም ሁለቱ ግዙፍ ኩባንያዎች በኢትዮዽያ ከዚ ቀደም ያልነበረ የቨርችዋል ቪዛ አገልግሎት አስጀምረዋል።
ከቨርችዋል ቪዛ ካርድ ባለፈ ሀዋላን የሚያቀላጥፉ አገልግሎት ለመጀመር ከቪዛ ኩባንያ ጋር ውል መታሰሩን ሰምተናል።
ስምምነቱ የቪዛ ዳይሬክት እና ቴሌብር ሬሚት የተሰኘ አገልግሎቶችን ለማቅረብ አስችሏል ተብሏል።
ከአለም አቀፉ ከቪዛ ኩባንያ ጋር የታሰረው ውል በኢትዮዽያ የመጀመሪያውን የዋሌት ቨርችዋል ቪዛ ካርድና ሀዋላን የሚያዘምኑ ቪዛ ዳይሬክት እና ቴሌብር ሬሚት የተሰኙ አገልግሎቶችን ይዞ በይፋ ወደ ስራ ገብቷል ተብሏል።
የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ “ ይህ ትብብር አስፈላጊው የቴክኖሎጂ ውህደትና ቅንጅት በሁለቱም ተቋማት በኩል ተጠናቆ ፤ ሙከራውና ፍተሻውንም በማለፉ ደንበኞች ተገልገሉበት“ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ “ ኩባንያው ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት በመሻገር የደንበኞች ቁጥሩ 78 ሚሊየን በመሆኑ ይህን አገልግሎ ለመጀመር ጉልበት ፈጥሮለታል፣ተመራጭና ተደራሽ እንዲሆንም ትልቅ አቅም ሆኖለታል“ ብለዋል።
ይህ ትብብር ከዚ ቀደም ከ 59 ሀገራት በቴሌ ብር አማካኝነት የሚገባውን ሬሚታንስ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግለትም ተሰምቷል ።
ኩባንያው ተቋማትም ግለሰብም በቀላሉ ገንዘብ መላላክ ሲችሉ ምህዳሩ ቀላል ይሆናል የንግድ ልውውጡም ይቀላጠፋል በማለት በ ቴሌ ብር የድንበር ተሻጋሪ የክፍያ ስርአትም እንዲኖር በብርቱ እየሰራሁ ነው ብሏል።
የቪዛ ካንትሪ ማናጄር አቶ ያሬድ እንዳለ በበኩላቸው “ወደ ፊት ወደ የትኛውም ሐገር ስንጔዝ አለም አቀፍ የዲጅታል ካርድ ሳንጠብቅ በቴሌብር ለመክፈል የምንችልበትን እድል ይዘን እንመጣለን” ብለዋል።
አቶ ያሬድ “ ትልቅ ግዙፍ ኩባንያዎች በጥምረት ሲሰሩ ብዙ ችግሮችን በመቅረፍ ትብብሩን ወደ ፊት እየቀጠልን እንድንሄድ ያስችለናል“ ብለዋል።
የቴሌብር ደንበኞች ቁጥር ብዛት 47.55 ሚሊዮን በላይ በመሆኑ ደንበኞች በቀላሉ የቨርችዋል ቪዛ ካርድ ቁጥር እንዲያገኙ እንዲሁም ከመደበኛው ሃዋላ የተሻለ አማራጮች በቪዛ ዳይሬክት እና ቴሌብር ሬሚት እንዲገለገሉበት ያግዛል ሲል ኩባንያው ተናግሯል።
የቪዛ ዳይሬክት አገልግሎት ከ190 በላይ ሀገሮች የሚኖሩ የቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች በሐገር ቤት የቴሌብር ቨርችዋል ቪዛ ካርድ ቁጥር በመጠቀም ገንዘብ ወደ ሀገርቤት በቅናሽ መላክ ያስችላቸዋልም ተብሏል።
ደንበኞች በቪዛ ዳይሬክት አገልግሎት ገንዘብ ለመቀበል ቅድሚያ የቴሌብር ሱፐርአፕ ከጫኑ በኋላ ለአገልግሎቱ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
ቀጥሎ ባለ 16 አሀዝ የቨርችዋል ቪዛ ካርድ ቁጥር ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የቴሌብር ሬሚት አገልግሎት ለማግኘት ደግሞ የ ሐገር ልጆች ባሉበት ሐገር ለግዜው ከአሜሪካ፣ ካናዳ፣ እስራኤል፣ ሳኡዲአረቢያ፣ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጣሊያን እና ስዊድን የቴሌብር ሬሚት መተግበሪያ መጫን አለባቸው ተብሏል።
በዚሁ አማካኝነትም ገንዘብ ለቴሌብር ደንበኞች በቀጥታ መላክ እንደሚችሉ ኩባንያው ተናግሯል።
አለም አቀፉ የገንዘብ አስተላላፊ ኩባንያ ቪዛ በጠቅላላ እስካሁን በዘረጋው መድረክ የ 160 ሀገሮችን ከረንሲ ወይም ገንዘብ ኦፕሬት እንደሚያደርግ ይታወቃል።
ተህቦ ንጉሴ
Comments