በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ኃይል ሊቋረጥ እንደሚችል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ተናገረ፡፡
የኤሌክትሪክ ሀይል የሚቋረጠው ወደ ተከዜ የኃይል ማመንጫ ግድብ የሚገባውን ውሃ በማስተንፈስ ሂደት የጣቢያው ዩኒቶች ሥራ በማቆማቸው ነው ብሏል፡፡
ከግድቡ ውሃ ሲለቀቅ የሚፈጠረው የእንፋሎት ጭጋግ በትራንስፎርመሮችና የኃይል ማመንጫ ቤቱ ላይ ጉዳት እንዳያስከትል ሁለቱ ዪኒቶች እንዲቆሙ ተደርጓል ተብሏል።
በዚህም የቮልቴጅ መዋዠቅ አጋጥሟል ብሏል ተቋሙ፡፡
በዚህ አጋጣሚ ከግድቡ በላይኛውና በታችኛው ተፋሰስ በሚገኙት፤
በጣንቋ፣ አበርገለ፣ በቆላ ተንቤን፣ በላዕላይ እና ታህታይ ማይጨው፣ በመረብለኸ፣ በአስገደ ጽንበለ፣ በላዕላይና ታህታይ አዲያቦ፣ በመደባይ ዛና፣ በታህታይ ቆራሮ፣ በአጠቃላይ የተከዜ ወንዝ ተዋሳኝ በሆኑ ወረዳዎች ነዋሪዎችና የመስተዳድር አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ተናግሯል ።
የክረምቱ ዝናብ እና ወደ ግድቡ የሚገባው የውሃ መጠን እስከሚቀንስ ድረስ ችግሩ ለቀናት እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comments