አዋሽ ባንክ በአምሪፍ ኸልዝ አፍሪካ እየተተገበረ ላለው ክፍታ ዩዝ ሳኮ የፋይናንሻል ቴክኖሎጂ በነፃ ማቅረቡን ተናገረ፡፡
ክፍታ ዩዝ ሳኮ ለወጣቶች ምቹ እና ተደራሽ የሆኑ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር አገልግሎቶችን በማቅረብ፤ የወጣቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ ማሻሻል ላይ የሚሰራ ፕሮጀከት መሆኑ ተነግሯል፡፡
ፕሮጀክቱ የተለያዩ የቁጠባና ብድር አሰራር በመዘርጋት ከአባላት ቁጠባ መሰብሰብ፣ የብድር አገልግሎት መስጠት እና ማስመለስ፣ አባላት ገንዘባቸውን አዋጭነት ባለው ስራ ላይ እንዲያውሉ የምክርአገልግሎት መስጠትና የአነስተኛ መድን ዋስትና አገልግሎት ለአባሉ መስጠትን እንደሚያካትት ሰምተናል፡፡
በUSAID 60 ሚሊዮን ዶላር ከሁለት ዓመት በፊት የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት ለ5 ዓመታት እንደሚተገበር ተነግሯል፡፡
ፕሮጀክቱ 2 ሚሊዮን ወጣቶችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ሲነገር ሰምተናል፡፡
ቢያነስ 50 አባላት ያሏቸው 13 የወጣቶች የህብረት ስራ ማህበራት እስካሁን መቋቋማቸው ተጠቅሷል፡፡
የህብረት ስራ ማህበራቱ የአባለት ምዝገባና አያያዝ፣ የብድር አገልግሎት አስተዳደር፣ እክሲዮን እና የአክሲዮን ክፍያ አገልግሎት፣ የምርት እና አገልግሎት ማኔጅመንት የመሳሰሉ ስራዎችን በዘመነ መልኩ አንዲሰሩ አዋሽ በንክ ስርዓቱን ማበጀቱ ሲነገር ሰምተናል፡፡
ይህ አዋሽ ባንከ በነፃ ተጠቀሙበት ያለው የቴክኖሎጂ ስርዓት 400 ሺህ ዶላር እንደሚያጣ ተጠቅሷል፡፡
የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት በውስጥ የአሰራር ደንባቸው መሰረት ለሚገባቸው ሰራተኞቻቸው ብቻ ስም እና የይለፍ ቃል በመስጠት መጠቀም የሚችሉበት አንደሆነም ተነግሯል፡፡
የማህበሩ አባላትም የቆጠቡትን ገንዘብ መጠን ማወቅ፣ የአክስዮን ድርሻ መጠንና እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments