ነሐሴ 2፣2015 - የኒጀር የመንግስት ገልባጮች ለሀገሪቱ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰየሙ
- sheger1021fm
- Aug 8, 2023
- 1 min read
በገልባጮቹ በጠቅላይ ሚኒስትር የተሾሙት ዓሊ ማሐማን ላሚን ዛይን እንደሆኑ ፒፕልስ ጋዜት ፅፏል፡፡
ላሚን ዛይን በተገለበጠው መንግስት የምጣኔ ሐብታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር እንደነበሩ ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኒጀር ፕሬዘዳንታዊ ዘብ የጦር ክፍል ባልደረቦች የፕሬዘዳንት ሞሐመድ ባዙምን መንግስት ከገለበጡት 2 ሳምንታት ሊሆናቸው ነው፡፡
ከስልጣን የተገለበጡት ፕሬዘዳንት አሁንም በገልባጮቹ እገታ ውስጥ ናቸው ተብሏል፡፡
የኒጀሩ ፖለቲካዊ ቀውስ ያለ ሁነኛ መፍትሄ እንደቀጠለ ነው፡፡
የኔነህ ከበደ

የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
コメント