top of page

ነሐሴ 21፣2016 - UNOPS ለሽሬው ስሁል ሆስፒታል ለጤና መርጃ መሳሪያዎች ግዥ ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ማድረጉ ተሰማ

በሰሜኑ ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመታት በፊት የተካሄደውን የርስ በርስ ጦርነት ተከትሎ በአለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግስት ስምምነት መሰረት በሶስተኛ ወገንነት የተመረጠው የመንግስታቱ ድርጅት ተቋም(UNOPS) ለሽሬው ስሁል ሆስፒታል ለጤና መርጃ መሳሪያዎች ግዥ ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ማድረጉ ተሰማ፡፡


የአፍሪካ ህብረት ወኪል እንዲሁም መቀመጫቸውን አዲስ አበባ በማድረግ የአካባቢ ሀገራትን በበላይነት የሚመሩት የተባበሩት መንግስታት የፕሮጀክት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ወርቅነሽ መኮንን ከጣሊያን ኤምባሲ ጋር ስለተደረገው ስምምነት ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነግረዋል፡፡


በሰሜኑ ጦርነት የደረሰውን የመሰረተ ልማት ውድመት ወደ ቦታው ለመመለስ በወቅቱ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለአምስት ክልሎች በአለም ባንክ በጀት መመደቡ የሚታወስ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለትግራይ ክልል ስለደረሰውና ስለዋለበት ስራም ወ/ሮ ወርቅነሽ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነግረዋል፡፡


በጦርነት የደረሰው የተቋማት ውድመትን ወደ ቦታው ለመመለስ የትግራይ ክልልን ብቻ UNOPS ሀላፊነትን ሲወስድ በሌሎች አራት ክልሎች የደረሰው ጥፋት ለመስራት የየክልል መንግስታቱ ሀላፊነት መውሰዳቸው ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ...


የኔነህ ሲሳይ

Commentaires


bottom of page