ለ1 ወር የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ይፋ አድርጓል።
በዚህም በምርቶቹ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።
በዚሁ መሠረት፦
በሊትር 69.52 ብር የነበረው ቤንዚን በ74.85 ብር ይሸጥ ተብሏል።
በሊትር 71.15 ብር ይሸጡ የነበሩት ነጭ ናፍጣ እና ኬሮሲን 76.34 ብር ሆነዋል።
የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 3.23 ጨምሮ 68.58 ብር ሆኗል።
ቀላል ጥቁር ናፍጣ ሊትሩ 62.22 ብር እንዲሁም ከባድ ጥቁር ናፍጣ 61.07 ብር ሆኗል።
ላለፉት 4 ወራት በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ ሳይደረግ መቆየቱን የጠቀሰው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሐምሌ ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳየ በመምጣቱ ዋጋውን ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉ ተናግሯል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments