‘’ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ’’ ተዋናይነት ፍናን ሂድሩን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መረጠ።
የአብሮ መስራት ስምምነቱ የአንድ ዓመት የሚቆይ ሲሆን፤ ፍናን ከኢንፊኒክስ ጋር በቅርበት በመስራት በተለይም ወጣቱን ከብራንዱ ጋር በማስተዋወቅ የራሷን ድርሻ ትወጣለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ፍናን በኢንፊኒክስ የተመረጠችው በፊልሙ ኢንደስትሪ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ያላትን ተቀባይነት እና ያላት የፈጠራ ችሎታ ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል።
ኢንፈኒከስ ከሚታወቅበት የስልክ ገበያ በተጨማሪ ወደ ቴሌቪዥን፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ኤር ፖድ እና መሰል ምርቶችን ወደ ገበያው ለማቅረብ ያለውን አላማ በመደገፍ ረገድ ተዋናይቷ ጉልህ ተሳትፎ ይኖራታል ተብሏል።
የኢኒፊኒክስ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር አቶ አሌከስ " ከታዋቂዋ አክተር ፍናን ሂድሩ ጋር አብረን ለመስራት በመቻላችን ድስተኛ ነን" ብለዋል፡፡
ፍናን በበኩሏ " ከዚህ ትልቅ ብራንድ ጋር አብሮ ለመስራት በመቻሌ አጅግ ደስተኛ ነኝ" ያለች ሲሆን "በአብሮነት ጎዞዋችን ተጠቃሚውን ከብራንዱ ጋር በማስተዋወቅ እና ከኢንፊኒክስ ምርቶች ጋር በማገናኘት የሚጠበቅብኝን ለመወጣት እሰራለሁ" ብላለች።
ኢንፊኒከስ አለም አቀፍ የኤሌከትሮኒከስ አምራች ኩባንያ ሲሆን በተለይም በሚያመርታቸው የስማርት ስልኮች አለም አቀፍ ተቀባይነትን ያገኘ ብራንድ ነው::
በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች አምራች የሆነው ''ኢንፊኒክስ'' አዲሱን "ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G" ስልኩን በኢትዮጵያ ገበያ በቅርቡ ማስተዋወቁ ይታወሳል።
የኢንፊኒክስ አዲሱ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ፤ ለጌመሮች እና ለሙዚቃ አድናቂዎች የተለየ ነገርን ይዞ መምጣቱ ተነግሮለታል።
Comments