በኢትዮጵያ በሚደርሱ ሰው ሰራሽም ይሁን የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የተጎጂዎችን ቁጥር አጋንነው የሚቀርቡ፤ የሚመደበውን እርዳታም ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉትን ተጠያቂ የሚያደርግ ፖሊሲ ሊፀድቅ ነው፡፡
ተደጋግመው እየደረሱ ያሉ የጎርፍና #የመሬት_መንሸራተት አደጋዎች፣ በየአካባቢው ባለው ግጭትና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እርዳታ ጠባቂ መሆናቸው ይነገራል፡፡
ለእነዚህ ተረጂዎች የሚመደብ የእለት ደራሽ #ምግብ እና ሌላውም ቁሳቁስ በአግባቡ መድረሱን የሚቆጣጠር አካል እስካሁን አልነበረም፡፡
ተረጂዎቹም በመገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ በቂ ድጋፍ አልተደረገልንም የሚል ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡
ለተረጂዎቹም እፎይታን የሚሰጥ፤ የሚመደበውን እርዳታም ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉ፤ የተረጂዎቹን ቁጥር አጋንነው የሚያቀርቡ የመንግስት ሹመኞችንና ባለሙያዎች በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ የፖሊሲ ረቂቅ መዘጋጀቱንና በቅርቡ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም ስራውን ሲጀምር እንደሚፀድቅ የፌድራሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አታለል አቡሃይ ለሸገር ተናግረዋል፡፡
ይፀድቃል በተባለው #ፖሊሲ አደጋዎች ሲከሰቱ ክልሎች በራሳቸው አቅም በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ መሆኑን የሚያነሱት አቶ አታለል እኛ ጣልቃ የምንገባው ክልሎች ከአቅማችን በላይ ሆኗል፡፡
ብለው ደብዳቤ ሲፅፉልን ነው፤ በየትኛውም የሃገሪቱ ማዕዘን የምንልከው እርዳታው በ72 ሰዓታት ይደርሳል ብለዋል፡፡
ለበርካታ አመታት ህይወታቸውን በእርዳታ እየመሩ ያሉ፣ በጊዜ ሂደት የገንዘብ አቅም ቢኖራቸውም እርዳታ ጠባቂ የሆኑ ሰዎችን እያፈራን ነው ብለዋል ሃላፊው፡፡
ባለሙያዎቹን እና #ሹመኞችን ከመቆጣጠር ባለፈ እርዳታውን የሚቀበሉ ሰዎችንም ለመቆጣጠር ሲባል በዲጂታል መንገድ ተመዝግበው እንዲወስዱ ለማድረግ እየሰፉ መሆኑን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አታለል አቡሃይ ነግረውናል፡፡
ከዚህ ቀደም ለተረጂዎች የተዘጋጀን የእርዳታ እህል መዝብረዋል በሚል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ኮሚሽነር በህግ ተጠያቂ መደረጋቸው ይታወሳል፡፡
ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ... https://tinyurl.com/93fdzx2r
ምንታምር ፀጋው
ቀደም ተብሎ የተሰራ ተያያዥ ዘገባን ለማድመጥ … http://surl.li/imugrz
Comments