top of page

ነሐሴ 26፣2015 - ሂጅራ ባንክ ኦምኒ ኘላስ (OmniPlus) የተሰኘ አገልግሎት ይፋ አደረገ



ባንኩ ኦምኒ ኘላስ የተሰኘውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቱን በተመለከተ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ላይ ይፋ አድርጓል።


ይህንን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያውን በመጠቀም ደንበኞች የገንዘብ መጠናቸውን ማወቅ ከመቻላቸው ባለፈ በባንኩ ውስጥ ባሉ አካውንቶች መካከል ወይም ወደ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ ማስተላለፍ የሚያስችል ነው ሲሉ የባንኩ ተጠባባቂ ኘሬዚደንት አቶ ዳዊት ቀኖ ተናግረዋል።


ቀሪ ሒሳብን ለማወቅ፣ የሒሳብ ሪፖርትን ማግኘት፣ ደንበኛው ከባንኩ ወደ ቴሌ ብር ገንዘብ ማስተላለፍና የአየር ሰአት ለመግዛት ያስችለዋልም ተብሎለታል።


መተግበሪያው በ6 ቋንቋዎች የቀረበ ሲሆን በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በሱማሌኛ፣ በአፋርኛ፣ በትግርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎችን መጠቀም እንደሚያስችል አቶ ዳዊት ተናግረዋል።


የዩኤስኤስዲ (USSD) የሞባይል ባንኪንግ እና የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎትን በአንድ መተግበሪያ መሆኑ ደግሞ የደንበኞችን የባንክ አጠቃቀም ምቹ ያደርገዋል ብለዋል።


ባንኩ በበጀት ዓመቱ የደንበኞቹን ብዛት ከ300 ሺህ በላይ ሲያደርስ 52 ቅርንጫፎችን በክልል ከተሞች እና በወረዳዎች፤ 19 ቅርንጫፎችን ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ በመክፈት አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሚገኝ አቶ ዳዊት ተናግረዋል።


ሂጅራ ባንክ ሙሉ በሙሉ ሸሪዓውን መሰረት ያደረገ የወለድ አልባ አገልግሎቱን ከነሐሴ 29 ቀን 2013 ጀምሮ እየሰጠ እንደሆነም ይታወሳል።



ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Коментарі


bottom of page