top of page

ነሐሴ 3፣2016የምግብ ዋስትና ችግር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተፈጠረው የእርስ በእርስ #ጦርነት እና የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ችግርን አክፍቶታል ተባለ፡፡


በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረው የሰላም እጦት አምራች የነበረውን ማህበረሰብ እንዳያመርት ስላደረገው የምግብ ዋስትናን እየፈተነው መሆኑን የግብርና ባለሙያው አቶ ሳለ ጌታሁን ይናገራሉ፡፡


ከሶስት አስርት አመታት በላይ በግብርናው ዘርፍ የሰሩት አቶ ሳለ ጌታሁን እንደሚሉት ከሆነ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአፈር መሸርሸር መጨመር፣ ሀገሪቱ ያላትን #የቀንድ_ከብት ባግባቡ አለመጠቀሟ፣ ባህላዊ የግብርና አስተራረስ ዘዴን መጠቀማችን፣ ድርቅ እና ሌላ ሌላውም ችግር ሲታከልበት፣ ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት የምግብ ዋስትና ማጣት ተዳርጋለች፡፡


በአለም አቀፍ ደረጃ እያጋጠመን ያለው #የአየር_ንብረት_ለውጥ ደግሞ ሌላኛው የምግብ ዋስትና ችግርን ከሚጨምሩን ነገሮች አንዱ መሆኑንም ነግረውናል፡፡


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እየታየ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ በተለይ በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ያሉ ሀገሮችን በእጅጉ እንደሚጎዱ ጥናቶች እያሳዩ መሆኑን የሚናገሩት የሚሉት አቶ ሳለ ጌታሁን እስከ 2030 ዓ.ም የእህል ምርቶች 30 በመቶ ይቀንሳሉ መባሉን ይቀንሳል ተብሎ እንደሚጠብቅ ጠቁመዋል፡፡


በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን #የምግብ_ዋስትና ችግርን ለመቀነስ ከተፈለገ ምን ዓይነት ስራዎች ሊከወኑ ይገባል? ከማንስ ምን ይጠበቃል?

የሀገር ውስጥ ምርትን በስፋት መጠቀም እና የግሉን ዘርፍ መደገፍ እንደሀገር ያጋጠመንን የምግብ ዋስትና ችግር ከምንፈታበት መንገዶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በተያዘው የፈረንጆች አመት 2024 በአፍሪካ ከሰሀራ በታች ከሚኖረው 20 በመቶው ህዝብ በልቶ ለማደር እየተቸገረ መሆኑ ይነገራል፡፡


በኢትዮጵያም ከ10 ሚሊየን በላይ ህዝቧ ኑሮው በሴፍቲ ኔት የተመሰረተና 5 ሚሊየን የሚሆነው ደግሞ በቀጥተኛ የእርዳታ እህል የሚተዳደር መሆኑን መጠቆሙ ይታወሳል፡፡



ፋሲካ ሙሉወርቅ



ተያያዥ ዘገባዎችን ለማግኘት እነዚህ ማስፈንጠሪያዎችን ይጫኑ..






የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page