top of page

ነሐሴ 30፣2016 - የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አሜሪካን በቀይ መስመራችን ላይ ባታላግጪ ይሻልሻል አሉ


የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አሜሪካን በቀይ መስመራችን ላይ ባታላግጪ ይሻልሻል አሉ፡፡


የላቭሮቭ ማስጠንቀቂያ የተሰማው አሜሪካ ለዩክሬይን ግዛት ተሻጋሪ ጥቃት መፈፀሚያ ሚሳየሎችን ማስታጠቅ በመቀጠሏ እንደሆነ አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡


የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሜሪካ የሩሲያን ቀይ መስመር ማለፏ ኋላ መዘዝ ያስከትላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡


ቀደም ሲልም የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን አገራቸው የታላቅ የኒኩሊየር የጦር መሳሪያዎች ባለቤት እንደሆነች ምዕራባዊያን ሊዘነጉት አይገባም ማለታቸው ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡


የላቭሮቭ ማስጠንቀቂያ 2 ሳምንታት ባልሞላው ጊዜ 2ኛቸው ነው ተብሏል፡፡



ቱርክ እና ግብፅ እኛው እንታረቅ ተባባሉ፡፡


የግብፁ ፕሬዘዳንት በይፋዊ ጉብኝት ቱርክ የገቡት ትናንት እንደሆነ ገልፍ ኒውስ ፅፏል፡፡


የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ለበርካታ ዓመታት ሻክሮ መቆየቱን መረጃው አስታውሷል፡፡


አሁን ግን መቃቃሩ ይብቃን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


የመከላከያ እና የኢነርጂ ዘርፎችን ጨምሮ 20 የትብብር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል ተብሏል፡፡


የሁለትዮሽ አመታዊ የንግድ ልውውጣቸውን 15 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ መስማማታቸውም ተጠቅሷል፡፡


ሁለቱ መሪዎች የአገሮቻቸውን የትብብር ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ቃል መገባባታቸው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡



ቻይና በአፍሪካ ተጨማሪ ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ነዋይ ስራ ላይ ልታውል ነው፡፡


ገንዘቡ ለተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንደሚውል የቻይናው ፕሬዘዳንት ሺ ጂን ፒንግ ለአፍሪካ መሪዎች ተናግረዋል፡፡


የቻይና እና የአፍሪካ የትብብር መድረክ በቤጂንግ እየተካሄደ መሆኑን TRT አፍሪካ ፅፏል፡፡


የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም በመድረኩ ተገኝተዋል ተብሏል፡፡


አዲሱ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ውጥን ቢያንስ 1 ሚሊዮን የስራ እድሎችን እንደሚያስገኝ ተነግሮለታል፡፡


በንግድ፣ በግብርና፣ በመሰረተ ልማት እና በሁለንተናዊ ዘርፎች ቻይና ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላት ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ ነው ተብሏል፡፡



የካሪቢያኗ ሀገር የሔይቲ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜውን ወደ መላው ሀገሪቱ አስፋፋው፡፡


አገሪቱ በተደራጁ የወሮበሎች ቡድኖች ተፅእኖ ሥርዓተ አልበኝነት ከሰፈነባት ቆይታለች፡፡


ለምሳሌም ከርዕሰ ከተማዋ ፖርቶ ፕሪንስ አብዛኛው ክፍል በወሮበሎቹ እጅ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ወሮበሎቹ ወደ ሌሎቹም ግዛቶች የመስፋፋት ሙከራ እያደረጉ ነው ተብሏል፡፡


መንግስትም የአስቸኳይ ጊዜውን ወደ ተቀሩት የአገሪቱ ክፍሎች ያስፋፋውም በዚሁ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል፡፡


የሔይቲው ሥርዓተ አልበኝነት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ማፈናቀሉ ይነገራል፡፡


የኔነህ ከበደ


Comments


bottom of page