በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች አምራች የሆነው ''ኢንፊኒክስ'' አዲሱን "ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G" ስልኩን በኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ።
የኢንፊኒክስ አዲሱ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ፤ ለጌመሮች እና ለሙዚቃ አድናቂዎች የተለየ ነገርን ይዞ መምጣቱ ተነግሮለታል።
የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ፤ 108 ሜጋ ፒክስል፣ ጥራት ያለው የካሜራ ቴክኖሎጂ ይዞ የመጣ ነው።
ከዚህ በተጨማሪም 100 ዋት ፈጣን ቻርጀር እና 20 ዋት ያለገመድ ዋየር ለስ ቻርጅ ማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተነግሮለታል፡፡
አዲሱ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ ስልክ፤ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ስፒከሮች የተገጠመለት ሲሆን 6.78 ኢንች ኦሞሌድ ዲስፕሌይ ከርቭድ ስክሪኑ ለተለያዩ ግልጋሎቶች ምቹ ያደርገዋል ተብሏል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Commentaires