top of page

ነሐሴ 7፣2016 - የኢንቨስትመንት ቢሮ የግል ትምህርት ቤቶችን ለመደገደፍ የህግ ማሻሻያ ባደርግም ብዙዎች እየተጠቀሙበት አይደለም ብሏል

የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ የግል ትምህርት ቤቶችን ለመደገደፍ የህግ ማሻሻያ ባደርግም ብዙዎች እየተጠቀሙበት አይደለም ብሏል፡፡


ሊጠናቀቅ አንድ ወር በቀረው 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ፍቃድ ወስደው ወደ ስራ የገቡ የግል ትምህርት ቤቶች ቁጥር 23 ናቸው፡፡


ነገር ግን ከነዚህ ውስጥ በቢሮው የሚሰጠውን ድጋፍ የወሰዱት ሁለት ብቻ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ይህንን የሰማነው ከአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ ነው፡፡


የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ ከዚህ ቀደም የግል ትምህርት ቤቶችን አስተዳድርበት የነበረው አዋጅ ክፍተት ስለነበረበት እሱ ተሻሽሎ ወደ ስራ ከገባ በኋላ ግን የሚነሱት ችግሮች እየተፈቱ ነው ይላል፡፡



Comments


bottom of page