top of page

ነሐሴ 8፣2016 - የስራ ግብር ምጣኔ ማሻሻያ ሳይደረግበት፤ ይደረጋል የተባለው የደመወዝ ማሻሻያ ምን ትርጉም ያመጣል?

በቅርቡ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዝቅተኛ ተከፋይን የመንግስት ሰራተኛ እንዳይጎዳ መንግስት የደመወዝ ማሻሻያ እንደሚያደርግ መናገሩ ይታወሳል፡፡


ሰራተኛው ከደመወዙ የሚቆርጥበት #የስራ_ግብር ምጣኔ ማሻሻያ ሳይደረግበት፤ ይህ ይደረጋል የተባለው የደመወዝ ማሻሻያ ምን ትርጉም ያመጣል?


ይህ የደመወዝ ማሻሻያው ለአንድ የመንግስት ሰራተኛ ከዚህ ቀደም ከሚያገኘው ክፍያ የተሻለ ይሆንለታል ተብሎ ቢታመንም በሚከፍለው የስራ ግብር መልሶ ሊያጣው ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡


ባለፉት ቅርብ ዓመታት የተሻሻለውና የወር ደመወዛቸው ከ10,900 ብር በላይ የሆኑ ሰራተኞች እስከ 35 በመቶ የስራ ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድደው #አዋጅ ሲተች መቆየቱ አይዘነጋም፡፡


ሰራተኛው ከሚያገኘው ደመወዝ ላይ ለመንግስት የስራ ግብር መክፈሉ ተገቢ ሆኖ ሳለ የስራ ግብር ጣሪያው ካልተስተካከለ አሁንም ገበያው ላይ መቆም አይችልም ተብሏል፡፡


ይህ ደግሞ የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ጋር የሚያያዝ ሲሆን አሁን ላይ በወር እስከ 600 ብር ገቢ ያላቸው ሰራተኞች ብቻ የገቢ ግብር የማይከፍሉ ሲሆን ከ10,900 ብር በላይ ገቢ ያላቸው ደግሞ 35 በመቶ ታክስ ይከፍላሉ ተብሏል፡፡


አንድ #የመንግስት_ሰራተኛ ደመወዙ 10,900 ብር ቢሆንና 35 በመቶ የስራ ግብር ሲቆረጥበት እጁ ላይ 7.085 ብር ይቀራል፡፡


ይህንን ይዞ ወደ ገበያ ሲቀላቀል ደግሞ ሻይ ሲጠጣ 15 በመቶ ቫት እንዲከፍል ይገደዳል፡፡


እንዲህ እንዲህ እያለ፤ በአጠቃላይ ከደመወዙ ግማሹ እንደሚቀነስበት የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ዋና ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ነግረውናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ.. https://tinyurl.com/3hr43jta


ማርታ በቀለ

Comments


bottom of page