ይህ የተባለው አዩቴ ኢትዮጵያ ቻሌንጅ ባዘጋጀው የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ነው።
አዩቴ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች 555 ከግብርና ስራዎች ጋር የተገናኙ የፈጠራ ስራ ያላቸው ወጣቶች ሲያወዳድር መሰንበቱን ሰምተናል፡፡
ተቋሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ግብርናው እንዲዘምንና ወጣቶች በዘርፉ እንዲሰሩ ቴክኖሎጂዎች ግብርናው ዘርፍ ላይ እንዲያዘምን እየሰራ መሆኑን ተናግሯል።
ለውድድር የሚቀርቡት ቴክኖሎጂዎችና የፈጠራ ስራዎች አነስተኛ ይዞታ ባለው ማሳ ላይ የተሻለ ምርት እንዲገኝ ማድረግን ለማስቻል ነውም ተብሏል፡፡
ከዚህ በፊት በ2ተኛው የአዩቴ ኢትዮጵያ ውድድር አሸናፊ የነበረው የስራ ፈጠራ ሀሳብ በአህጉር አቀፍ በተካሄደው አዩቴ አፍሪካ ቻሌንጅ አሸንፏል።
የፈጠራ ስራው እንደ አፍሪካ የሚታየው #የአፈር_ማዳበሪያ ችግርን ይፈታል ተብሎ የታለመለት ኦርጋኒክ የአፈር ማዳበሪያ ማምረት ነው።
አሁን በተደረገው የ3ተኛ ዙር እዩቴ አፍሪካ ቻሌንጅ 555 የሚሆኑ የግብርናንውን ዘርፍ የሚያዘምኑ ስራዎችና የቴክኖሎጂ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን በዳኞች ውሳኔ 3 ፈጠራ ስራዎች አሸናፊ ሆነዋል።
የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በበኩሉ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር ስራ ፈጣሪ ወጣቶች በብዛት እንዲወጡ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል።
የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በመወከል ንግግር ያደረጉት ብርሃኑ አደሬ፤ ከተባባሪዎቹ ውጪ በራሱ በ3 ዙሩ 1375 የፈጠራ ስራ ያላቸው ሰዎች በዚህ አመት ያውዳደረ ሲሆን አሁን 400 የሚሆኑት ተለይተዋል ይላሉ።
ከዚህ ውስጥ 50 የሚሆኑት የስራ ፈጠራዎች አሸናፊ እንደሚሆኑና ስራቸው ወደ ተግባር እንደሚገቡ ይደረጋል ብለዋል።
እንደ አዩቴ ያሉ ተቋማት በተለይም ግብርናው እንዲዘምን የሚያደርጉት ስራ አድንቀው በተለይም የፈጠራ ስራ እንዲስፋፋና ግብርናው እንዲዘምን እየሰሩት ያለው ስራ መንግስት ይደግፈዋል ይላሉ።
ለአሸናፊዎሽም ስራቸው ወደተግባር እንደሚደረግና ከዚህ በፊት ያሸነፉት የስራ ፈጣራ ወጣቶች እየተከታተሉ መሆኑን ተናግረዋል።
አዩቴ ኢትዮጵያ ቻሌንጅ ላይ የሚሳተፉት እድሜያቸው ከ18 እስከ 30 ያሉ ወጣቶች ነው።
አዩቴ ኢትዮጵያ ቻሌንጅ ላሸነፉ ተወዳዳሪዎች 20,000 የአሜሪካ ዶላር እንደተሸለሙ ተመልክተናል፡፡
በረከት አካሉ
Comments