top of page

ከተተከሉ ችግኞች ምን ያህሉ እንክብካቤ አግኝተው ፀደቁ የሚለው ትኩረት ሲሰጠው አይታይም


ክረምት በመጣ ቁጥር ከፍተኛ ሀብት እየፈሰሰ በቢሊዮን የሚቆጠር ችግኝ ይተከላል፡፡


ከተተከሉ በኋላ ምን ያህሉ እንክብካቤ አግኝተው ፀደቁ የሚለው ግን ትኩረት ሲሰጠው አይታይም፡፡


ይህ መስተካከል ያለበት ነው የሚሉት የዘርፉ ባለሙያዎች የት ቦታ ምን መሳይ ዝርያ ያለው ችግኝ ይተከል የሚለውንም መለየት ያስፈልጋል ይላሉ፡፡


በአብዛኛው የሚተከሉ ችግኞች መጤ መሆናቸውም ሊጠፋ የተቃረቡ ሃገር በቀል ችግኞች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑንም ሸገር ያነጋገራቸው ተመራማሪ ተናግረዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page