ከጋዜጠኝነት ስነ -ምግባር ውጭ መረጃዎችን የሚያሰራጩ የመገናኛ ብዙኃን
- sheger1021fm
- Jun 29, 2023
- 1 min read
መገናኛ ብዙሃን ለህዝብ የሚያቀርቡት መረጃ የሞያውን ስነ ምግባር የጠበቀ ካልሆነ ከጥቅማቸው ይልቅ ጥፋታቸው እንደሚበረታ ይታወቃል፡፡
ኢትዮጵያም በዚህ ፈተና ውስጥ ያለች ትመስላለች፡፡
የሀሰት መረጃ በመፈብረክ ጥላቻ የሚያራገቡ ፤ ከጋዜጠኝነት ስነ -ምግባር ውጭ የብሔርና የሃይማኖት ፀብ የሚጭሩ መረጃዎችን የሚያቀርቡ በርክተዋል ተብሏል፡፡
በዚህም የዜጎች የሰብአዊ መብት አያያዝ አደጋ ላይ ወድቋል ይላል የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትቶች ኮሚሽን፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤትም ችግሩ የበረታ መሆኑን ጠቅሶ እንዲሰተካከል ስልጠና ከመስጠት ጀምሮ ተጠያቂ እስከማድረግ የሚደርስ ስራ እየከወንኩ ነው ብሏል፡፡
ፍቅሩ አምባቸው
#Ethiopia#ShegerFM####
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments