የሸገር የምሳ ሰዓት ወሬዎች - ታህሳስ 23፣2016
- sheger1021fm
- Jan 2, 2024
- 1 min read
#ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ትናንት በአዲስ አበባ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ በርካታ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የተለያዩ ዘገባዎችን እያወጡ ነው፡፡
20 ኪሎ ሜትር የባህር መተላለፊያ ለመጠቀም የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ለሶማሌላንድን የነፃ አገርነት እውቅናን እንደምትሰጥ ተነግሯል፡፡
#የወደብ ባለቤት መሆን የባህር በር መውጫ ማግኘት፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ አጠቃላይ ወጪና ገቢ ንግዱ ላይ ሊያመጣ የሚችለው ምንድነው?
የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
#በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልዩ ወረዳ ይሰጠን ጥያቄ ባነሱ የጋሞ ዞን ነዋሪዎች እና በዞኑ አስተዳደር መካከል የተፈጠረው ግጭት ሳይባባስ መላ እንዲሰጠው ተጠየቀ፡፡
በግጭቶች ሰዎች እየተገደሉ መሆኑን እና የተፈናቀሉም ስለመኖራቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናግሯል፡፡
#አፍሪካዊያን እርስ በእርስ ያለ ቀረጥ ይገበያዩበታል የተባለው እና ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ስራ እንደሚገባ ተነግሮለት የነበረው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ከሙከራ የዘለለ ተግባር አልታየበትም፡፡
ይሁንና ወደ ስራ ሲገባ ጀማሪ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ጫና እንዳይበረታባቸው የሚያስችል አሰራር እንደሚዘረጋ የንግድና ቀጠና ትስስር ሚንስቴር ተናገረ፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments