የነሐሴ 24፣2015 የባህር ማዶ ወሬዎች
- sheger1021fm
- Aug 30, 2023
- 1 min read
የፍልስጤም ራስ ገዝ አስተዳደር በዌስት ባንክ እስራኤላዊያን ሰፋሪዎች ተጨማሪ ህገ-ወጥ ኬላዎችን እያቆሙ ነው አለ፡፡
አስተዳደሩ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አማካይነት የእስራኤላውያን ሰፋሪዎችን ተጨማሪ ኬላ ማቆም እንዳወገዘው ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡
ዌስት ባንክ የፍልስጤማውያን ይዞታ መሆኑ ቢታወቅም በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን በዚያ እንደሚኖሩ ይነገራል፡፡
በአሁኑ ወቅት የእስራኤላውያን የሰፈራ መንደሮች መስፋፋት በዌስት ባንክ ግጭት እና ፍጥጫውን እያባባሰው ነው ተብሏል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዌስት ባንክ የሚገኙ የእስራኤላውያን የሰፈራ መንደሮችን ህገ-ወጥ ናቸው እንደሚል ዘገባው አስታውሷል፡፡

ሩሲያ ዩክሬይን የሰደደችብኝን አውሮፕላን መሰል አጥቂ ሰው አልባ በራሪ አካል /ድሮን/ አወደምኩት ማለቷ ተሰማ፡፡
ዩክሬይን ድሮን ለጥቃት የተላከው በጥቁር ባህር ወደሚገኝ የሩሲያ ይዞታ ነበር መባሉን አናዶሉ ፅፏል፡፡
አውሮፕላን መሰሉ ድሮን አሜሪካ ስሪት ነው ተብሏል፡፡
ዩክሬይን ከቅርብ ወራት ወዲህ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት እየሰነዘረች መሆኑ ይነገራል፡፡
ሩሲያም አብዛኞቹን ድሮኖች ከዒላማቸው ሳይደርሱ አክሽፌያቸዋለሁ እያለች ነው፡፡
የትናንቱን የአውሮፕላን መሰል ድሮን ማውደም በተመለከተ ከዩክሬይንም ሆነ ከአሜሪካ በኩል የተሰጠ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ የለም ተብሏል፡፡

እስራኤል ከሊባኖስ በኩል የሚሰነዘርብኝን የጠብ አጫሪነት አስታግስልኝ ስትል ለተባበሩት መንግስታት አስታግስልኝ ስትል ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አቤት ማለቷ ተሰማ፡፡
እስራኤል በሰሜናዊው ወሰን ፀብ አጫሪነት እየተፈፀመብን ነው ማለቷን አናዶሉ ፅፏል፡፡
ለጠብ አጫሪነቱ የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ሄዝቦላህ የተሰኘውን የሊባኖስ የጦር እና የፖለቲካ ድርጅት መክሰሳቸው ተሰምቷል፡፡
የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ሊባኖሳውያን ወሰን አልፈው በግዛታችን ድንኳን እስከምትከል ደርሰዋል ብለዋል፡፡
የእስራኤል የሊባኖሳዊያኑን ጠብ አጫሪነት አስታግሱልን አቤቱታ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መላኩ ታውቋል፡፡
በዚህ ጉዳይ የሊባኖስ አስተያየት በዘገባው አልተጠቀሰም፡፡

የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments