የካቲት 1፣2016 - ተለዋዋጭ የሆነው የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ሁኔታ እና የኢትዮጵያ የውጪ ፖሊሲ
- sheger1021fm
- Feb 9, 2024
- 1 min read
ኢትዮጵያ የምትከተለው የውጪ ፖሊሲዋ ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጥ እና በእኩል ተጠቃሚነት መርህ ላይ ትኩረት ያደረገ ቢሆንም ከጎረቤቶቹ የሚገኘው ምላሽ ከኢትዮጵያ የሚቀርበውን ያህል አለመሆኑ ይነገራል፡፡
በተለይም ተለዋዋጭ በሆነው የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ሁኔታ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶቿን የዲፕሎማሲዋ መነሻና መደራደሪያ ጉዳይዋ ልታደርግ ይገባል የሚሉ ባለሙያዎች አሉ፡፡
የቀጠናው የዲፕሎማሲ ሁኔታ በፍጥነት የሚለዋወጥ በመሆኑ እሱን መሰረት በማድረግ ለሀገር ጥቅም መስራት ይገባል ተብሏል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
コメント