top of page

የካቲት 12፣2016 - የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ኢትዮጵያ 4 ስምምነቶችን እንድታፀድቅ ጠየቀ

ስምምነቶቹ ከፀደቁ በስራ ቦታ እና የቤት ሰራተኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ለማስቆም ይረዳሉ ተብሏል።

 

4ቱ ስምምነቶች ‘’189 የቤት ሰራተኞች መብት የሚያስጠብቅ ኮንቬሽን፣ 190 የስራ ቦታን ፆታዊ ትንኮሳን እና ጥቃትን መከላከል እና ማስወገድ ኮንቬሽን፣ 97 እና 143 ፍልሰተኛ ሰራተኞችን አስተዳደር ኮንቬሽን’’ ተብለው የሚጠሩ መሆናቸወን ሲነገር ሰምተናል፡፡

 

በኢትዮጵያ በቤት ሰራተኝነት  የሚሰሩ ሰራተኞች ከፍተኛ አካላዊና ፆታዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው የተናገሩት የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ናቸው።

 

አሁን እንዲፀድቁ እየተጠየቁ ያሉት ስምምነቶች በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞችን መብት የሚያስጠብቁ ናቸው ብለዋል።

 

ኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞችን የሚመራ ህግ የላትም የተባለ ሲሆን ይህ ሰምምነት ሰራተኞቹን እና አሰሪዎቹን የሚጠቅም ነው ሲሉ አቶ ካሳሁን አስረድተዋል።

 



በስራ ቦታ የሚታዩ ጥቃቶችን ለመከላከል የወጣው ስምምነት የሚፀድቅ ከሆነ በስራ ቦታ የሚታዩ ፆታዊና አካላዊ ጥቃቶችን ለመከላከል ይረዳል ተብሏል።

 

በተለያዩ አለማት የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች በአሰሪዎቻቸው የሚደርስባቸውን ጥቃትና እንግልት የሚያስቀርና መብታቸው እንዲከበር የሚረዳ መሆኑንም ሲነገር  ሰምተናል።

 

 

ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በህጋዊ መንገድ ሰራተኞችን ወደ ውጪ ሀገራት እየላከች መሆኑ ጥሩ ቢሆንም አሁን እንዲፀድቁ የተጠየቁት አለማቀፍ ስምምነቶች ካልፀደቁ የሰራተኞችን መብት ለማስከበር ይከብዳል ተብሏል።

 

4ቱ ስምምነቶች የሀገሪቱ የሕግ አካል እንዲሆኑ እና ተግባራዊ እንዲደረጉ የሚያስችል የግንዛቤ ፈጠራ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ሕግ አውጪዎች፣ የዓለም ሥራ ድርጅት ተወካይ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና የአሠሪ ተወካዮች በተገኙበት እተካሄደ ነው፡፡

 

 

በረከት አካሉ

 


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

Comentários


bottom of page