top of page

የካቲት 13 2017 - ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ምክክሩ አለመግባታቸው በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ምክክሩ የተሟላ እንዳይሆን ሊያደርግ ይችላል ተባለ

ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ምክክሩ አለመግባታቸው በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ምክክሩ የተሟላ እንዳይሆን ሊያደርግ ይችላል ተባለ፡፡


ይህን ያለው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነው፡፡


ባለፈው ማክሰኞ አንድ ዓመት ተጨማሪ የስራ ዘመን የተሰጠው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይህን የተናገረው ዛሬ በቦሌ ስካይ ላይት ሆቴል ለጋዜጠኞች የሶስት ዓመት የስራ ክንውኑን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡


የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የሀገራዊ ምክክሩ ሙሉ እንዲሆን ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች መሳተፍ አለባቸው ብለዋል፡፡


በሀገሪቱ ህጋዊ ፍቃድ አግኝተው ከሚንቀሳቀሱ ወደ 70 ከሚጠጉ የፖለቲከ ፓርቲዎች ውስጥ 57 የሚሆኑት አብረውን እየሰሩ ነው ሲሉ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ተናግረዋል፡፡


በ10 ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ከ1 ሺህ 260 በላይ አጀንዳዎችን ከህብረተሰቡ ላለመግባባት እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮች በመሆናቸው እንዲፈቱ ሲሉ አጀንዳ አድርገው ሰጥተውኛል ሲል ኮሚሽኑ ተናግሯል፡፡


በአማራ ከ8 ወረዳዎች ውጪ የተሳታፊ ልየታ ማድረጉን የተናገረው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተጨመረለት 1 አመት ውስጥ አጀንዳ ማሰባሰቡን እንደሚያጠናቅቅ አስረድቷል፡፡


የሀገራዊ ኮሚሽን ኮሚሽነር መስፍን አርአያ ለትግራይ ክልል ኮሚሽኑ ምንም ዓይነት ስራ አለመጀመሩን ተናግረው በተሰጠን አንድ ዓመት የስራ ዘመን በትግራይ ክልል የምክክር እና የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እናጠናቅቃለን ብለዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page