በአለም ከአንድ መቶ በላይ ሀገሮች የሆቴል አገልግሎት የሚሰጠው ሒልተን ሆቴል በአዳማ እና በድሬደዋ ሆቴሎች ሊከፍት መሆኑ ተሰማ፡፡
ሆቴሎቹ ከ3 ዓመት በውሀላ በአዳማ እና በድሬዳዋ ይከፈታሉ መባሉን ኦል አፍሪካ ፅፏል።
ኩባንያው በኢትዮዽያ የተለያዩ ስምንት ንብረቶችን ለማስተዳደርም በእቅዱ አስፍራል።
ደብል ትሪ ባይ ሂልተን የተሰኝው ብራንድ ከ24ቱ በሂልተን ከሚተዳደሩ ሆቴሎች አንደኛው ነው።
በአዳማ የሚገነባው ይህ ሆቴል ከአዲስ አበባ ጋር በሚያገናኘው ዋና መንገድ ላይ የሚሰራ ነው ተብሏል፡፡
በአዳማ የሚሰራው ደብል ትሪ ባይ ሂልተን 188 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች ይኖሩታል ሲል የወሬ ምንጩ ዘግቧል፡፡
የድሬዳዋው ድግሞ 150 የእንግዳ ማረፊያ ይኖሩታል ተብሏል፡፡

ሁለቱም የሂልተን ሆቴሎችና ሰፊ ማረፊያዎች ለተጓዦች እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ከፍ ያለ የምግብ እና የመጠጥ አማራጮችን ይሆናሉ።
ሂልተን በተለያዩ ሀገሮች ቅንጡና አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቁ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሆቴሎች እንዳሉት ይታወቃል።
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments