ባንኩ አገልግሎቱን በይፋ ያስጀመረው በድሬደዋ ከተማ ባዘጋጀው ስነ ሥርዓት ላይ ነው፡፡
በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የወጋገን ባንክ ኢንተርፕራይዝ አገልግሎቶች ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ የኋላሸት ዘውዱ ወጋገን ሞባይል መተግበሪያ ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
መተግበሪያው ደንበኞች ከባንክ ወደ ባንክ ገንዘብ ማስተላለፍ እና ክፍያዎችን በምቹ ሁኔታ ለመፈፀም ያስችላል ብለዋል፡፡
ደንበኞች የወጋገን ሞባይል መተግበሪያን ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር በማውረድ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡
መተግበሪያው በአምስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ እና በሶማልኛ ይሰራል ተብሏል፡፡
ባንኩ እንደ አማራጭ ደንበኞች በማንኛውም ዓይነት ስልክ ወደ *866# በመደወል በአማርኛና በእንግሊዝኛ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቱን ያለ ኢንተርኔት መጠቀም እንደሚችሉ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው አስረድተዋል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments