የኢሜግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ኢ-ፓስፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡
የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርቱ የግለሰቦችን መረጃና የጣት አሻራ የያዘ የኤሌክትሮኒክ ችፕስ የያዘ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
አዲሱ ፓርፖርት በአገር ውስጥ የታተመና ከፍተኛ የደህንነት ደረጃ እንዳለው ሰምናል፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ ኢ-ፓስፖርት የኢሜግሬሽን ሒደት የሚያቀላጥፍ እንደሆነ ሰምናል፡፡
በሃገር ውስጥ የሚታተመው ፓስፖርቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን መመዘኛዎች ያሟላና አለም አቀፍ ተቀባይነትን ያረጋገጠ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የኢሜግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለውጭ አገር ዜጎች የሚሰጠውን ቪዛ በአዲስ ህትመት እና ይዘት በአገር ውስጥ ታትሞ አገልግሎት ላይ እንደሚውል ሰምተናል፡፡
የኢሜግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በስራ ላይ የነበረው የአስቸኳይ የጉዞ ሰነድ በወረቀት ይታተም የነበረ በመሆኑ የሌላ አገር ዜጎች ስደተኛ ነን በማለት ከአገር ይወጡበት እንደነበር መናገሩ ይታወሳል፡፡
ይህ አሰራር አሁን ላይ ወደ ዲጂታል መቀየሩን ተከትሎ ተመሳሳይ ማጭበርበር እንደማይኖር ከኢሜግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሰምተናል፡፡
ኢ-ፓስፖርቱ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በቶፖን ሴክዩሪቲ ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር አማካኝነት አገር ውስጥ መመረቱን ሰምተናል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments