top of page

የካቲት 14 2017 - ያልሆኑትን ሆንን እያሉ ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያሻሽጡ ድርጅቶች መበርከታቸውን የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ተናገረ

ያልሆኑትን ሆንን እያሉ ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያሻሽጡ ድርጅቶች መበርከታቸውን የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ተናገረ፡፡


የሀገር ውስጥ አምራቾች የሚያመርቱት ምርት የጥራት ደረጃቸው በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ አያደርጋቸውም ተብለዋል፡፡


ድርጅቱም ‘’የሚሞቱ ሰዎች የማይሞት ተቋምን መስርተው እንዲያልፉ ነው ጥረት እያደረኩ’’ ያለሁት ሲል ተናግሯል።


የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ መብራት በኢትዮጵያ ያሉ አብዛኞቹ አምራቾች የሚያመርቱ የምርት የጥራት ደረጃቸው ባለማቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን የማይችሉ መሆናቸውን አንስተው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት እየሰራ ያለው የ #ጥራት ደረጃን ያሟሉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ተቋማትን ማስፋፋት ላይ ነው ብለዋል።


ለጥራት ሽልማት ማወዳደር ብቻ ግባችን አይደለም የሚሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ዋናው ግባችን የምናወዳድራቸውና ሽልማት የምንሰጣቸው ድርጅቶች በጥራት እና በልህቀት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ሆነው የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲያሻሽሉ ማስቻል ነው ሲሉ ይናገራሉ።


አምራች ድርጅቶች ለምርት ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ጥራትን ባህል ማድረግ እንዳለባቸው የሚያነሱት አቶ ቴዎድሮስ ይህ ካልሆነ ግን ጫናው መልሶ አምራቾቹ ላይ ያርፋል በምርጥ ጥራት ችግርም ተጠቃሚ በማጣት ድርጅቶች እስከመዘጋት ድረስ ሊያደርሳቸው እንደሚችልም ጠቁመዋል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ ….


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page