የካቲት 17 2017 - በአዲስ አበባ ከተማ በሸቀጦች ላይ የዋጋ መናር በተዳዳሚ ይስተዋላል
- sheger1021fm
- Feb 25
- 1 min read
በአዲስ አበባ ከተማ በሸቀጦች ላይ የዋጋ መናር በተዳዳሚ ይስተዋላል፡፡
ሸገር ራዲዮ በተለይ ስለ ዘይት ዋጋ ማሻቀብ እና በአንዳንድ ቦታዎች ምርቱ ከገበያ የመጥፋቱ ምክንያት ምንድነው ሲል የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮን ጠይቋል።
እንደማሳያም 5 ሊትር #ዘይት ከሁለት ሳምንታት በፊት ሲሸጥ ከነበረው ከ1100 እስከ 1200 በአንዴ ከ1480 እስከ 1700 ሲሸጥ ተመልክተናል፡፡
በአንዳንድ ሱቆች ደግሞ ምርቱ ስለተወደደ ከናካቴው መያዝ መተዋቸውን ነግረውናል፡፡
በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች አምስት ሊትር ዘይት ከ1480 እስከ 1700 ብር፣ ሶስት ሊትር ከ850 እስከ 900 ብር፣ አንድ ሊትር ደግሞ ከ300 እስከ 350 እተሸጠ እንዳለ ነጋዴዎቹ ነግረውናል፡፡
በሁለት ሳምንት ልዩነት በምግብ ዘይት ምርት ላይ እንዲህ ያለ የዋጋ ጭማሬ ማሳየቱ ለምን ይሆን፡፡
መፍትሄውስ ምንድነው ያልነው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የዋጋ ጭማሪው በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ለማወቅ ጥናት እያደረኩ ነው ብሏል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments