የካቲት 20፣2016 - የሰላም ሚኒስቴር በ45 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከጥር 9 ጀምሮ በሶስት ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጉን ተናገረ
- sheger1021fm
- Feb 28, 2024
- 1 min read
ርዕሰ ጉዳዮቹ በሀገራዊ ጥቅም፣ ሀገራዊ እሴት እና የጋራ ማንነት ናቸው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ያህል በሀገራዊ ጥቅም ያምናል፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ብሔሮች የራሳቸው እሴት እንዳላቸው ሁሉ በሀገራዊ እሴት ያምናሉ ወይ፣ ካላቸው የተለያየ ማንነት ባለፈ አንድ በሚያደርግ የኢትዮጵያ ማንነት ላይ ያላቸው አመለካከት ምን ይመስላል? በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ሲሉ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የሰላም ሚኒስትር ድኤታው ከይረዲን ተዘራ አስረድተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን እና ወጣቶች በ45ቱም የትምህርት ተቋማት ተሳትፈዋል ብለዋል፡፡
ተደርጓል በተባለው የውይይት መድረክ ከ20 ሺህ በላይ መምህራን እንደተሳተፉና የትምህርት ተቋማቱ ባላቸው የማህበረሰብ ሬዲዮ ለ40 ሚሊየን ሰዎች ተደራሽ ማድረግ ችለዋል ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል፡፡
በውይይቱና በምክክሩ ላይ የተገኙት ውጤቶች አርብ በአድዋ ሙዚየም ይፋ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡
ያሬድ እንዳሻው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Kommentare