top of page

የካቲት 20 2017 - የኢትዮጵያ ገንዘብ የመግዛት አቅም ከጀመረው የቁልቁለት ጉዞ የማቆሚው መላ ምን ይሆን?

ከዶላር አንፃር የኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ የመግዛት አቅም ከጀመረው የቁልቁለት ጉዞ የማቆሚው መላ ምን ይሆን?


የብር የመግዛት አቅም ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከመቶ በመቶ በላይ ወርዷል፡፡


ገበያ መር ነው የተባለው የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት የነበረው አንድ የአሜሪካን ዶላር የመሸጫ ዋጋ ከነበረበት 57 ብር ወደ 127 ብር ከፍ ብሏል፡፡


ለሁለተኛ ዙር የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞ እለት ብሄራዊ ባንክ በገበያው ላይ ያለውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ለማሻሻል በሚል በጨረታ የሸጠው 60 ሚሊዮን ዶላር የተገዛበት የአንድ አሜሪካን ዶላር አማካኝ ዋጋም የብር የመግዛት አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ጊዜ መንሸራተቱን በግልጽ የሚያሳይ ሆኗል፡፡


በመጀመሪው ዙር ብሄራዊ ባንክ አውጥቶት በነበረው ጨረታ በአማካኝ አንድ የአሜሪካን ዶላር የተሸጠበት ዋጋ 107 የነበረ ሲሆን የካቲት 18 ቀን ለሁለተኛ ዙር በቀረበው ጨረታ እና 27 ባንኮች እንደተሳተፉበት በተነገረው ላይ ደግሞ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ135.61 ብር ተሽጧል፡፡


ለመሆኑ ከ90 በመቶ በላይ የመሆኑት ባንኮች አንድ የአሜሪካን ዶላር 135.61 ተጫርተው የገዙት ገንዘብ ኖሯቸው ነው? አትርፈው ለመሸጥስ ግዢ አግኝተው ነው? የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም የመድክም ጉዞ ማብቂውስ የት ነው ?

ሁለት የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያዎችን ጠይቀናል፡፡


ብሔራዊ ባንክ ከወርቅ ሽያጭ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢ እያገኝ መሆኑን እና በዛው ልክ ደግሞ ወርቅ ለመግዛት ከፍተኛ ብር ወደ ገበያው እያፈሰሰ ስለሆነ ወደ ገብያው የፈሰሰው ብር ደግሞ የዋጋ ንረቱን እንዳያባብስ ዶላርን ለባንኮች በጨረታ በማቅረብ ከገበያው ላይ ብርን ለመሰብሰብ እና ገበያውን ብር ለማስራብ ብሄራዊ ባንክ ዶላርን ለጨረታ እንዳቀረበ የፋይናስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያ እና አማካሪው አቶ ጥላሁን ግርማ ያስረዳሉ፡፡


አቶ ጥላሁን ለባንኮች በጨረታ የተሸጠው 60 ሚሊዮን ዶላር ባንኮች ያለባቸውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ከመፍታት አንፃር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው በማስረዳት በሀገሪቱ ካሉ ባንኮች ውስጥ ከ90 ከመቶ በላይ የሚሆኑት መሳተፋቸው እና ዝቅተኛ ሀብት ያላቸው ባንኮች የተሻለ የሃብት አቅም ካላቸው ባንኮች ጋር እኩል ተወዳድረው መጫረታቸው ግን ጤናማ አካሄድ አልመሰለኝም ብለዋል፡፡


ባንኮች በግዙበት ዋጋ አትርፈው ለመሸጥ ገዢ ያገኛሉ ወይ ስንል አቶ ጥላሁን ጠይቀናል፡፡


ባንኮቹ ተጫርተው አንድን ዶላር በ135 ብር ከ61 ሳንቲም በገዙበት ማግስት የባንኮችን የምንዛሪ መሸጫ ተመልክቼ ነበር በዚህም በአማካንኝ በአንድ ዶላር ከ10 ብር በላይ ጭማሪ እያደረጉ ገዝተው በመሸጥ ላይ ያሉት ከጭረታው በፊት ከነበረው ብዙውም ልዩነት የለውም ማነው በ20 ሺህ ብር የተገዛን በግ በማግስቱ 15 ሺህ ብር የሚሸጠው ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡


ይህም ምናልባት የተወሰኑ ባንኮች ከዚህ ቀደም የውጭ ምንዛሬ ፈቅደው መክፈል ያቃታቸው እዳ አለባቸው ብዬ አስባለው እንዳን ለመክፈል ደግሞ በየትኛውም ያክል ገንዘብ ከሚወጣ ጭረታ ገዝተህ ለመክፍል ትገደዳለህ ሲሉ አስረድተዋል፡፡


ለባንኮች በጨረታ የተሸጠው 60 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለመቆጣጠር እና ለማረጋጋት የጥቁር ገበያ ለማጥበብ እንደሚረዳ በማስረዳት የሚጀምሩት የፋይናነስ እና ኢንቨስትመንት በለሙያው አቶ ከፈለኝ ኃይሉ በተለይ ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ዋጋቸው እንዲንር እንደሚደርግ አስረድቷል፡፡


በአቶ ታምራት ሀሳብ የማይስማሙት አቶ ከፈለኝ ሃይሉ ባንኮች በጨረታ የገዙት የውጭ ምንዛሬ ውድ ቢሆንም ገዢ አያጡም ይላሉ ምክያቱም ካለፉት ሶስት ዓመታት ጀምሮ የተከማቸ ውጪ ምንዛሪ ፍላጎት እንዳለ በማስረዳት፡፡


አቶ ከፈለኝ የዶላር ዋጋ በዚሁ ከቀጠለ የብር የማግዛት እቅም እየደከመ እንደሚሄድ ለዋጋ ንረቱም መባበስ ምክንያት እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡


የሀገሪቱን ገንዘብ የማግዛት አቅም ከቁልቁለት ጉዞ ለመታደግ ድግሞ የውጭ አልሚዎችን መሳብ ከውጭ የሚገቡ እቃዎችን መቀነስ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ማሳደግ ትውልደ ኢትዮጵያን በአገራቸው እንዲያለሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ከፈለኝ ሃይሉ አስረድተዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page