top of page

የካቲት 20፣2017 - ዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸመ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ተዘግቧል

በዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸመ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ጠቅሶ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡


በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት የቆሽት እና የሐሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊቲ ሐኪም ተመራማሪ መምህር እና በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ባልታወቁ ኃይሎች መገደላቸው ይታወሳል።


የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፖሊስ ባደረገው ክትትል አንደኛውን ተጠርጣሪ ገዳይ በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል ብለዋል።


እሱባለው ነበረ የሚባል ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል ነው ያሉት።

ወንጀል ፈጻሚው ድርጊቱን መፈጸሙን ማመኑንም ተናግረዋል።


ግድያው ጥቅም ፍለጋ መሆኑን ተናግረዋል።


ፖሊስ የዶክተር አንዱዓለም ዳኘን ገዳዮች ለፍርድ እንደሚያቀርብ ቃል በገባው መሠረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ነው ተናግሯል።


በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ተመሳሳይ ወንጀሎችን ይፈጽም እንደነበርም አንስተዋል።


በግድያ ወንጀሉ ከተሳተፉት ውስጥ የተያዘው ተጠርጣሪ ዋናው መኆኑን የተናገሩት ኃላፊው እርሱን ያገዙ እና ግብረ አበሮቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ፖሊስ እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል።


ማርታ በቀለ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page