top of page

የካቲት 21፣2016 - በሰሜን አዲስ አበባ መውጫ አዲሱ ገበያ አካባቢ በ200 ሚሊዮን ብር የተገነባ ሆቴል ለአገልግሎት ክፍት ሊሆን ነው

በሰሜን አዲስ አበባ መውጫ አዲሱ ገበያ አካባቢ በ200 ሚሊዮን ብር የተገነባ ሆቴል ለአገልግሎት ክፍት ሊሆን ነው።


ናሁ ሰናይ የተሰኘው ይህ ሆቴል የ’’ናሁ ሰናይ የዘይት ማምረቻ’’ እህት ድርጅት እንደሆነም ተነግሯል፡፡


ለ15 ዓመታት ገደማ በምግብ ዘይት ማምረት ስራ ላይ የቆየው ናሁ ሰናይ የንግድ ድርጅት ‘’ናሁ ሰናይ ሆቴል’’ን ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ለማወቅ ችለናል፡፡


ሆቴሉ የተለያዩ የመንግስት አካላትና እንግዶች በተገኙበት በመጪው ቅዳሜ የካቲት 23 ይመረቃል ተብሏል፡፡



200 ሚሊዮን ብር ለሆቴሉ ግንባታ ወጣ የተባለ ወጪ ሲሆን ግንባታው 3 ዓመታት መውሰዱንም የሆቴሉ ባለቤት አቶ እሱባለው ናሁሰናይ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡


በአዲስ አበባ አዲሱ ገበያ ሸገር መናፈሻ አከባቢ የተገነባወ ናሁሰናይ ሆቴል፤ ቦታው ነፋሻማ እና ተስማሚ አየር ያለበት በመሆኑ እንደመረጡትም አቶ እሱባለው ተናግረዋል፡፡


የሆቴሉ ባለቤት አቶ እሱባለው የንግድ ድርጀታቸው በቀጣይም ሌሎች ሆቴሎችን የመገንባት እቅድ እንዳላቸውም የጠቆሙ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የሚጠበቅባቸው ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡


የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ካሳሁን፤ ሆቴሉ ከ70 እስከ 100 ለሚደርሱ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሮላቸዋል ብለዋል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


bottom of page