በአዲስ አበባ በመጪው ዓመት የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለትምህርት ለመመዝገብ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ወይንም ፋይዳ መያዝ አስገዳጅ ሆነባቸው፡፡
የከተማው ትምህርት ቢሮ የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ይፋ አድርጓል ተብሏል።
ተማሪዎች የፋይዳ ምዝገባ አንዲያካሂዱ በዘመቻ መልክ ለመሰራት የታሰበ ሲሆን እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በላይ የሆናቸው ህፃናትን ምዘገባ በዘመቻ እንደሚከናወን ተነግሯል።

የፋይዳ ምዝገባ ቁጥር በአዲስ አበባ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት በቅድመ ሁኔታነት የተቀመጠ ሲሆን በከተማው ያሉ የመንግስት ሰራተኞች የቅጥር እና ዝውውር እንዲሁም የደመወዝ አከፋፈል ስርዓት ከምዝገባ ስርዓቱ ጋር እንዲቀናጅ በአስገዳጅ ስርዓትነት መቀመጡን ሰምተናል፡፡
የከተማዋ ትምህርት ቢሮ የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ቅድመ ሁኔታም እንደሆነ ይፋ አድርጓል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments