top of page

የካቲት 21 2017 - ''ከግብር አከፋፈል ጋር በተያያዘ ያነሳነው ጥያቄ ምላሽ አልተሰጠንም'' የትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን

የትራንስፖርት ሰጭ ድርጅቶች ለመከላከያ ሰራዊት ለሰጡት አገልግሎት እስካሁን አስፈላጊው ክፍያ እንዳልተከፈላቸው የትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ተናገረ፡፡ 

 

ፌደሬሽኑ ለመከላከያ ሚኒስቴር ለሰጠነው የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያው ሙሉ በሙሉ ካልተፈፀመልን ጉዳዩን ወደ ህግ እንወስደዋለንም ብሏል።

 

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን አባላት ከወራቶች በፊት በትራንስፖርቱ ዘርፍ ላይ አሉብን ያሏቸውን ችግሮች በተመለከተ የጋራ አቋም መግለጫ አውጥተው ነበር። 

 

በመግለጫውም ዘጠኝ ዋና አባይት ጉዳዮችን አንስተዋል።

 

ለአብነት አሽከርካሪዎች በታጣቂ ሀይሎች ግድያና እገታ እየተፈጸመባቸው ነው፣ በክልል ከተሞች በህገወጥ መንገድ ኬላ በመዘርጋት የሚጠየቅ የኮቴ ክፍያ፣ የጅቡቲ መንገድ መበላሸትና ተጽዕኖው፣ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሰጠነው የትራንስፖርት አገልግሎት አልተከፈለንም የሚል እና ሌሎችም ጉዳዮች ይገኙበታል።

 

 እኛም ፌዴሬሽኑ ያነሳቸውን ጥያቄዎች መዘገባችን ይታወሳል።

 

ለመሆኑ ፌዴሬሽኑ ያነሳቸው ቅሬታዎች እና ችግሮች ምን ያህሎቹ እልባት አግኝተው ይሆን?  ምላሽ ያልተሰጠባቸው ጉዳዮችስ የትኞቹ ናቸው? ብለን ለኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኔ ዘርኡ ላነሳንላቸው ጥያቄዎች በህገወጥ መንገድ ኬላ በመዘርጋት የሚጠየቅ የኮቴ ክፍያ፣ በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደርስ እገታ እና ግድያ  ቀንሷል ብለውናል።

 

በጅቡቲ መግቢያ የነበረው የመንገድ ብልሽት እልባት አግኝቷል ሲሉ ነግረውናል።

 

አቶ ብርሀኔ አክለውም አሉብን ያልናቸው ችግሮች አብዛኞቹ መፍትሄ እያገኙ ቢሆንም ከ #ግብር አከፋፈል ጋር በተያያዘ ያነሳነው ጥያቄ ምላሽ አልተሰጠንም ብለዋል።

 

 

 ሌላኛው እስካሁን መፍትሄ አልተገኘም የተባለው ጉዳይ ደግሞ ለመከላከያ ሚኒስቴር የተሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ አንዱ መሆኑን አቶ ብርሃኔ ነግረውናል።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…



 

ፍቅሩ አምባቸው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

 

Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page