በነገው ዕለት የሚከበረውን 128ኛው ዓመት የዓድዋ ድል ምክንያት ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ተናገረ፡፡
የድል በዓሉ በአዲስ አበባ ፒያሳ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚከበር ተነግሯል፡፡
በዓሉ በሚከበር ዕለት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ለተሽከርካሪ ዝግ የሞሆኑ መንገዶችን ፖሊስ አስረድቷል፡፡
• ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ
• ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ
• ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ
• ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ
• ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ
• ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከአገር አስተዳደር መብራት( ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማ መብራት
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች ነገ የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ/ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ ከዋዜማው ከዛሬ የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች እና ፕሮግሙ በሚካሄድበት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ዙሪያ ተሽከርካሪን ማሳደርም ሆነ ለአጭርም ሆነ ለረጀም ሰዓት አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑንም ፖሊስ አሳስቧል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentários