አቢሲኒያ ባንክ አለም አቀፉን የሴቶች ቀን (March 8 ) ምክንያት በማድረግ እችላለሁ በሚል መሪ ቃል ለ4ተኛ ጊዜ የሴቶች የተሰጥኦ እና የስራ ፈጠራ ዕድል ዉድድር መረሃ ግብር አስጀምሯል::
ባንኩ ከዚህ ቀደምም እንዲህ አይነት ዉድድሮችን ማዘጋጀቱን እና የአሁኑ ለአራተኛ ጊዜ የተሰናዳ መሆኑን ተናግሯል፡፡
በዚህም የእችላለው መረሐ ግብር በሙዚቃ፣ በድምፅ፣ በቲክቶክ ቪዲዮ እና በስራ ፈጠራ ውድድሮች ላይ ተስጥዖ ያላችሁ እንስቶች ተሳተፉ ብሏል፡፡
በሙዚቃ፣ በድምፅ እና በአጭር የቲክቶክ ቪዲዮ አሸናፊ ሆነው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለሚወጡ ሴቶች ከሃምሳ ሺ ብር እስከ አንድ መቶ ሺ ብር የሚደርስ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ከባንኩ ሰምተናል፡፡
በሚሰሩት አጭር የቲክቶክ ቪዲዮ የተስጥዖ ውድድር ባንኩ ለሴት ደንበኞች ያዘጋጀውን አደይ እና ዘሃራ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎቶችን በተለየ መንገድ ማስተዋወቅ እንዳለባቸው ተናግሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊ ለሚሆኑ 50 ሴቶች ለስራ ማስፋፍያ የሚሆን በአነስተኛ የወለድ ምጣኔ ካለመያዣ እስከ አምስት መቶ ሺህ የብድር አገልግሎት እሰጣለሁ ብሏል፡፡
የመወዳደሪያ ሥራ ማስረከቢያ ጊዜ ከየካቲት 24 እስከ መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ሥራ በባለሙያና በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የሕዝብ ድምጽ ተለይቶ አሸናፊዎች የሚለዩ ይሆናል ተብሏል፡፡
በዚህ የ4ኛ ዙር የእችላለሁ ውድድር ሴት ደንበኞችን እና ከባንኩ ብድር ወስደው ሥራቸውን ማስፋፋትና ሕይወታቸውንም መቀየር የቻሉ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ሥራቸውን የሚያስተዋውቁበትና ለሽያጭ የሚያቀርቡበት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የንግድ ትርዒትና ባዛር እንደሚየሰናዳ ባንኩ ተናግሯል፡፡
ይህ የሽያጭ ዘመቻ የባንኩን 'አደይ' እና 'ዘሃራ' የሴቶች የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎቶችንና ተያያዥ ባህሪያቱን ለማስተዋወቅ፣ በሴቶች ጉዳይ ላይ ከሚሠሩ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር፣ በአነስተኛ የንግድ ሥራ ላይና በሥራ ፈጠራ ላይ የተሰማሩ ሴቶችን ወደ ባንካችን ለማምጣት ያግዛል ተብሎለታል፡፡
በተጨማሪም አቢሲንያ ባንክ ከወጣቶች ጋር ያለው ግንኙነት ከፍ እንዲል፤ የባንኩን ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ለማሳደግና አዳዲስ ደንበኞች እንዲመጡ ለማድረግ፣ እንዲሁም ማኅበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ያግዛል መበሉን ሰምተናል፡፡
ባለፉት ሦስት ዓመታት በተከናወኑት የእችላለሁ የሽያጭ ዘመቻዎች ባንኩ ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ለ 1125 ሴት ደንበኞች ያለዋስትና በመስጠት የሴት ደንበኞቹን ወደ ተሸለ ስኬት ለማምጣት ሲሰራ መቆየቱን ተናግሯል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments